August 25, 2013
አምባገነኑ የህውሃት ኢህአዲግ አገዛዝ አገራችን ኢትዮጵያን ላለፉት ሀያ ሁለት አመታት በጎሳ በቋንቋና በሃይማኖት ለመከፋፈል ሆድ አደር ተላላኪዎቹን አስርጎ በማስገባት ዜጎችን እርስ በርስ በመከፋፈል ሰይጣናዊ እኩይ አላማውን በማካሄድ ላይ ይገኛል። ጉዳይ አስፈጻሚው የሆኑትን ሆድ አደር ግለሰቦች በሀይማኖት ተቋማት ውስጥ ሳይቀር አስርጎ በማስገባት ይቅር የማይባል ከፍተኛ በደል በመፈጸም ላይ ይገኛል።
እነዚህን ሆድ አደር ወገኖች የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን ጠንቅቆ ሊያውቃቸው ይገባል። ወያኔ በዋልድባ ገዳም እና በመነኮሳቱ ላይ እያደረሰ ያለውን ዘግናኝና አላፊነት የጎደለውን ተግባር ለማውገዝና ከአድራጎታቸውም እንዲታቀቡ የሚጠይቁ ምእማናን የተቃውሞና የተማጽንኦ ጥሪያቸው እንዳይሳካ ለማድረግ ሆድ አደሮቹ ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም፤ አሁን ደግሞ ከአሳዳሪዎቻቸው በሚሰጣቸው መመሪያ መሰረት፦ ጠንካራ እንቅስቃሴና የተቀናጀ የአንድነት ሕዝባዊ ትግል አሁን በጋራ በማድረግ ላይ የሚገኙትን የእስልምና እና የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ምእመናንን አንድነት ለማጥፋት በግራኝ መሀመድ ዘመን የፈረሱ ቤተክርስቲያኖችን ለማሳደስ ገንዘብ አዋጡ በሚል ሰበብ፤ የወቅቱን ሁኔታ ያላገናዘበና ባደፈ ቃላት የተደረተ መሰሪ በራሪ ወረቀት ሰሞኑን እየበተኑ መሆኑን ተረድተናል።
ይህ አፍራሽና ከፋፋይ ተልእኳቸው በቃ መባል ያለበት ጉዳይ ሲሆን፤ በዲሲና አካባቢው የምትገኙ ምእመናንም የነዚህን የወያኔ መራሽ አፍራሽ ተላላኪዎችን ከፋፋይ ሴራ ለማስወገድ በቆራጥነት እንድትታገሉአቸው በልዑል እግዚአብሄር ስም እናሳስባለን። አገራችን ኢትዮጵያን ከበግ ለምድ ለባሽ የቀበሮ ባህታዊያን አምላክ ይጠብቅ።
አገራችን ኢትዮጵያን እና ህዝቧን አምላክ ይባርክ!!!
ከአገር ወዳድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ምእመናን
ዋሽንግተን ዲሲ
No comments:
Post a Comment