Saturday, May 17, 2014

ናይሮቢ ላይ ፍንዳታ ደረሰ

ኬንያ ናይሮቢ ውስጥ ዛሬ ብዙ ሕይወት ያጠፋና ሌላም ጉዳት ያደረሰ ከባድ ፍንዳታ ደርሷል፡፡
አሜሪካና እንግሊዝ ሰሞኑን ለዜጎቻቸው የጉዞ ማስጠንቀቂያ ያወጡ ሲሆን ግን የናይሮቢ ባለሥልጣናት ግን ይህንን እርምጃቸውን ወቅሰው መግለጫ አውጥተዋል፡፡ 
በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ስድስት መቶ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሃገር መመለሱን አስታውቋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ኬንያ ውስጥ በስደተኞች ላይ እየተካሄደ ያለው ከበባና ማሳደድ አያያዝ እንደሚያሳስባቸው አንድ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ ገልፀዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢትዮጵያዊያኑ ወደ ሃገር እንዲመለሱ የሚደረገው በግዴታ ነው የሚሉ ኬንያ ውስጥ የሚገኙ ስደተኞች አሉ፡፡

No comments:

Post a Comment