Sunday, April 6, 2014
ሰበር ዜና - ኢህአዲግ/ወያኔ የኖርዌይ ዜግነት ያለውን ትውልደ ኢትዮጵያዊ የቀድሞ የጋምቤላ ክልል አስተዳዳሪ ኦኬሎ ኦቻላን ከደቡብ ሱዳን ጋር በመተባበር ጠልፎ ወደ ኢትዮጵያ በመውሰዱ ከኖርዌይ መንግስት ጋር ዲፕሎማሳዊ ፍጥጫ ውስጥ ገብቷል።ኢህአዲግ/ወያኔን ''ድንበር ተሻጋሪ አሸባሪ'' ለመሆኑ ይህ በቂ ማስረጃ ነው የሚሉ አሉ።
የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዝዳንት ኦኬሎ ኦቻላን በታህሳስ/1996 ዓም (ዲሴምበር 13/2003 እ አ አቆጣጠር) በጋምቤላ በተፈፀመው ጭፍጨፋ ወቅት ከሀገር መውጣታቸው እና በተለያዩ ሃገራት ከኖሩ በኃላ ወደ ኖርዌይ በመምጣት ዜግነት ማግኘታቸው ይታወቃል።
ሐሙስ መጋቢት 25/2006 ዓም ከ 150 ዓመት በላይ በሕትመቱ ዓለም መቆየቱ የሚነገርለት የኖርዌይ ቁጥር አንድ ተነባቢ ጋዜጣ ''አፍተን ፖስተን'' ''ትውልደ ኢትዮጵያዊው ኖርዌጃዊ ከደቡብ ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ካለፈቃዱ ተወሰደ'' በሚል አርዕስት ስር ባስነበበው ዘገባ ስር ጋዜጣው ዜናውን ሲቀጥል '' የሰብአዊ መብት አክቲቪስት'' በማለት የጠራቸውን አቶ ኦከሎ ኦቻላ በደቡብ ሱዳን መንግስት ባለስልጣኖች አጋዥነት ወደ ኢትዮጵያ ተወስደው እንዲታሰሩ መደረጋቸውን እና ኖርዌይ ጉዳዩን አዲስ አበባ በሚገኘው ኢምባሲዋ እየተከታተለች መሆኗን ጋዜጣው ያብራራል።
ሚስተር ስቫየን ሚቸልሰን የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኮምንኬሽን ጉዳዮች አማካሪ ስለ ጉዳዩ የሚከተለውን ብለዋል ''He confirmed that Aquai (ኦኬሎ) is a Norwegian citizen and that UD is familiar with the matter . The Norwegian Embassy in Addis Ababa now assisting Aquai''
''Han bekrefter at Aquai er norsk statsborger og at UD er kjent med saken. Den norske ambassaden i Addis Abeba bistår nå Aquai, opplyser Michelsen, som ikke ønsker å si noe mer om saken.''
'' ኦኮሌ የኖርዌይ ዜግነት ያለው ግለሰብ ነው።የኖርዌይ የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ (UD) የእርሱን ጉዳይ በሚገባ ያውቀዋል።አዲስ አበባ የሚገኘው የኖርዌይ ኤምባሲ ለኦኬሎ ድጋፍ እያደረገ ነው'' ሲሉ ባጭሩ ማብራራታቸውን ጋዜጣው ያትታል።
በመጨረሻም ጋዜጣው ኦኬሎ በሰብአዊ መብት ጥሰት በደረሰባት ጋምቤላ በነበረው ችግር መሰደዳቸውን ገልጦ የደቡብ ሱዳን የፀጥታ ኃይሎች ግለሰቡን ከደቡብ ሱዳን እና ዑጋንዳ ድንበር መካከል መወሰዳቸውን ያብራራል።
ጉዳዩን እዚህ ኖርዌይ ውስጥ የተመለከቱ ተንታኞች ኢህአዲግ/ወያኔን ''ድንበር ተሻጋሪ አሸባሪ'' ለመሆኑ በቂ ማስረጃ መሆኑን ይስማማሉ።
በእርግጥም ነገሩን ስናጤነውም ኖርዌይ በጋምቤላ ጉዳይ የመግባት እድሏን በሰፊው የሚከፍትላት ከመሆኑም በላይ ዜጋዋን በነፃ በማስለቀቁ ሂደት ላይ ከኢህአዲግ/ወያኔ ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በፍጥነት ሊያሽቆለቁል እንደሚችል ብዙዎች ያምናሉ።
ኢህአዲግ/ወይኔ እጅግ ከሚፈራቸው እና ''ስስ ብልቶቹ'' ተብለው ከሚጠቀሱት ጉዳዮች አንዱ የጋምቤላው እልቂት ሳብያ በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት የመከሰስ እድሉ ሰፊ የመሆኑ እውነታ መሆኑ ይታወቃል።
ጉዳያችን
መጋቢት 26/2006 ዓም
ኦስሎ፣ኖርዌይ
የ ''አፍተን ፖስተን'' ጋዜጣ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ያወጣውን ዘገባ ዕትም ከእዚህ በታች ይመልከቱ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment