መጋቢት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የፐብሊክ ዲፕሎማሲና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ጄኔራል አቶ ጌታቸው አረዳ እንደተናገሩት ” የኤርትራ መንግስት ሃሳቡን ቀይሮ ወደ ሰላም ቢመጣ የኢትዮጵያ መንግስት ችግር የለበትም። የኤርትራ ተቃዋሚዎች ከጉያችን ስላሉ ምን እንሆናለን የሚል ስጋት የለብንም” በማለት ተናግረዋል።
የታጠቁ የኤርትራ ሃይሎች እርምጃ የማይወስዱት በድንበር አካባቢ የኤርትራ ሰራዊት በብዛት ስላለ መሆኑን የገለጹት ጄኔራል ዳይሬክተሩ፣ የኤርትራ መንግስት ከእኛ ጋር ለመስማማት ከፈለገ ምንም ቂምና ቁርሾ የምንይዝበት ነገር አይኖርም ሲሉ አክለዋል።
ኢትዮጵያ 20 ሺ ኤርትራውያን ስደተኞችን ታስተምራለች የተባለውም የተጋነነና ቁጥሩ ከ1800 እንደማይበልጥ የተናገሩት አቶ ጌታቸው፣ እነዚህ ተማሪዎች የጸጥታ ስጋት እንደማይሆኑና አስፈላጊው ምርመራ ተካሂዶባቸው ትምህርት እንደጀመሩ ገልጸዋል።
ከኤርትራ ስደተኞች ይልቅ የጸጥታ ስጋት የሚፈጥረው የኢትዮጵያ ተስፋ የቆረጠው ወጣት ነው ያሉት አቶ ጌታቸው፣ ይህን ወጣት መከታተል የጸጥታ ችግሮችንእንደሚቀርፍ ገልጸዋል።
በንግግራቸው መሃል ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ባይከብርም የመክፈር ፍላጎት እንዲኖረው በማድረጋችን ጸጥአየትኩረት አቅጣጫውን ለማስቀየር ችለናል ብለዋል።
የጅቡቲ ወደብን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ደግሞ፣ ለጅቡቲ ወደብ የምንከፍለውን ኪራይ የጅቡቲ መሪዎች ቤተሰቦች የሚቀራመቱት በመሆኑ አገሪቱ ወደብ ትከለክለናለች ብለን አንሰጋም ሲሉ መልሰዋል።

No comments:
Post a Comment