ባለፈው ሐሙስ በሜሪላንድ የኢሳት 3ኛ ዓመት በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል። በዚህ የኢሳት 3ኛ ዓመት ላይ በተደረገ የገቢ ማሰባሰብ ቁጥሩከወትሮው በዛ ያለ ሕዝብ የተገኘ ሲሆን ለኢሳት ያለውን አጋርነት አሳይቷል። ከጨረታ እና ከአዳራሽ መግቢያም ከ60 ሺህ ዶላር በላይ እንደተገኘም አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በዚህ የኢሳት በዓል ላይ ከተጋበዙ ተናጋሪዎች መካከል የግንቦት 7 መሪ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከሰሞኑ እየተነሳ ከሚገኘው “ኢሳት የማነው?” ጥያቄ ጋር በተያያዘ የ21 ደቂቃ ንግግር አድርገዋል። ዘ-ሐበሻ በካሜራዋ