Wednesday, May 29, 2013

በነጭ ውሸት ላይ የተመሰረተ ትንተና የት ያደርሰን ይሆን?


በቴዎድሮስ በላይ
አቶ ጁዋር ሲራጅ መሃመድ በቅርቡ ከአቶ ደረጀ ደስታ ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስበአጽንኦት ተከታትያለሁ። የሰውየው ግለ ታሪክና ያደረጋቸው ጉዞዎች መሳጭ ቢሆኑም አንዳንድ እርማት የሚያስፈልጋቸው የተሳሳቱና የተዛቡ ታሪኮችን እንደገና እንዲፈትሽ፤ ሆን ብሎ እያራገበው ከሆነም ቆም ብሎ እንዲያስብበት ለመጠቆም ወደድኩ። የተሳሳተ መረጃ መረጃ ራስንም ሌላውንም ክፉኛ ይጎዳል። ሊዘህ መነሻ የሆነኝ፤ ስለ ኦሮሞ ጭቆና መነሻውን ሲገገልጽ፤ አማራዎቹ የአውሮፓን መሳሪያ ቀድመው ስላገኙ የሚል፤ መሰረት የለሽ ውንጀላው ነው።
ጋዜጠኛ ደረጀ ስለ ኦነግ አመሰራረት ሲጠይቀው፤ ጁዋር እንዲሚከተለው መለሰ።  “እንግዲህ በመቶ አመታት ወደዃላ ሂደን ስናይ አካባቢው በቡድን ግጭት የተሞላ ነበር-በተለይ ከ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወዲህ። ከዚያ በፊት አብዛኛው የሐይማኖት ነበር። በሐይማኖት ስር የተደራጁ መንግስታት ነበር ሲጋጩ የነበሩት። ከዚያ በዃላ ግን የብሔር ግጭቶች ነበሩ። ይህ የብሔር ግጭት፤ በአማራ፣ በኦሮሞና በትግሬ የተካሄደው ነው-ኢትዮጵያን የወለደው። በዚህ ግጭት ውስጥ ቀድሞ የአውሮፓን መሳሪያ ሊያገኝ የቻለው የአማራው ሀይል አሸንፎ፤ በበላይነት አሁን የምናውቃት ኢትዮጵያን ፈጠረ። “  እጅግ በጣም የገረመኝ መልስ ነው። በእርግጥ አቶ ጁዋር ብቻ አይደለም ፤ በቅርብ ጊዜ የምሰማው ከመሰሎቹ የኦሮሞ ወንድሞቼ የዕለት ከዕለት ውንጀላ ሆኗል። ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል፤ እንዲሉ የዚህ አይነቱን ነገር እንደ እውነት ሳይወስዱት አልቀረም።
ይሄ መልስህ፤ ብዙ ጥያቄዎችን አጭሮብኛል፡
  • በውኑ ኢትዮጵያን የወለደ ከ14ኛው አመት በዃላ ያለው የብሔር ግጭት ነው?
  • ከ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በነበሩት የሐይማኖች ግጭቶች፤ የኦሮሞ ሕዝብ የት ይሆን የነበረው?
  • በውኑ አማራው ነው የውጭዎቹን መሳራያውን ቀድሞ ያገኘው? ማረጋገጫ ልትሰጠኝ ትችላለህ? እኔ ያነበብሁትና የማውቀው ሌላ ነው።
ለምን የፈጠራ ውንጀላ ውስጥ በተለይ ማንበብና መጻፍ ከምንችል ሰዎች መካከል እንደምንዘፈቅ አይገባኝም። ሁለቱን ጥያቄዎች ለአቶ ጁዋር ትቼ፤ ለውንጀላ የተጠቀምህበትን ሶስተኛውን ጥያቄ እኔው ካነበብሁት እመልሳሃለሁ። ስህተት ከሆነ ማስረጃ ያቅርብና እንከራከርበት። ኢትዮጵያውያን እርስ በራሳቸው፤ በአካባቢያቸው በሰሩት መሳሪያ ይዋጉና አሸናፊው ይገዛ እንደነበር የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። በዚህ እርሱ እና እኔም እንስማማለን።  እንዲህ አይነቱ ልማድ በሌሎቹም አለም ሲደረግ የኖረ ሃቅ ነው። ነገር ግን የአለም ሁኔታ ተቀይሮ፤ አንዱ የሌላውን  ሃብት ድምበር አቋርጦ ለመዝረፍ ሲባል፤ ጠመንጃ መሳሪያን ይዘው ብቅ አሉ።   በመሰረቱ የጠመንጃ መሳሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጠረው  በ14ኛው ክፍለ ዘመን በቻይናዎች ነው። ወዲያውኑም ወደ ሩቅ ምስራቆችና አውሮፓዎቹ ተዛመተ። አውሮፓውያንና ሩቅ ምስራቆች፤ በሐይማኖት ሰበብ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭትን አስነሱ፤ የጠበንጃ መሳሪያውንም ይዘው ተነሱ። በኢትዮጵያም ይኸው ሆነ። በወቅቱ፤ ከክርስቲያኖች ጋር ለተጣላው ግራኝ አህመድ፤ ቱርኮቹ ልዩ ሰልጠና ሰጥተው የጦር መሳሪያ አስታጥቀው፤ ከሰለጠነ ወታደር ጋር  ወደ ኢትዮጵያ አስገቡት፤ በ11529 ጀምሮ ኢትዮጵያን በይፋ ወረረ። በጦርና በጨበጣ ብቻ የመዋጋት ልምድ የነበራቸው ኢትዮጵያውያን፤ የጠመንጃ መሳሪያ የታጠቀውን መሃመድን በምንም መልኩ ሊቆጣጠሩት አልቻሉም። ብዙ የሰው ህይወትና የአገር ሃብት አወደመ። በወቅቱ የነበሩ ገዥዎች፤ እርሱን ለመቋቋም፤ ክርስቲያን ክፍል የሆኑትን ፓርችጋሎችን በመማጸን የመሳሪያና የሰው ሃይል እርዳታ አግኘተው፤ ተዋግተው አሸነፉ። ይህ ነው የጠመንጃ መሳሪያ ወደ ኢትዮጵያ አመጣጡ። ይሄን እውነታ ቀይሮ አማሮቹ መሳሪያ ቀድሞ ስላገኑ የሚለው አካሄድ፤ ምን አይነት የፓለቲካ ትርፍ ያመጣ ይሆን? በመሰረቱ፤ የግራኝ ጦርነትን ተከትሎ ሰሜኑን የወረረው ማን ነው። የኦሮሞዎች ወረራና በቀላሉ ሰፊውን የሃገሪቱ ክፍል የመያዝ ውጤቱ፤ በግራኝ አማካኝነት የተካሄደው ጭፍጨፋ ከፍተኛ የሆነውን የአማራ  ሕዝብ ስለጨረሰ ነው። ለዚህ መከራከሪያ ምላሹን ከአቶ ጁዋር እፈልጋለሁ። የኦሮሞ ማህበረሰብ በወቅቱ የተፈጠረውን አጋጣሚ በመጠቀም፤ የሰሜኑን ክፍል ወርሮ ያሸነፈው ብቸኛው ምክንያት ይሄው ነው። የጦር መሳሪያ ወደ ኢትዮጵያ መግባት የጠቀመው፤ አቶ ጁዋር  እንደጠቀሰው አማራውን ሳይሆን ኦሮሞውን ነው። ከቆላማው ወደ ደጋማውና ለም የሃገሪቱ ክፍል እንዲገቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጎላቸዋል።  ይሄን ጥሬ ሃቅ ክዶ፤ በወቅቱ የተሰራን ግፍ ወደ ሌላው መለከክ፤ ከአንድ የፓለቲካ ተንታኝ፣ ያውም ሌሎቹን እያሰለጠነ ካለ በፍጹም አይጠበቅም።
በወንድሜ፤ በአቶ ጁዋር አካሄድ ቢተነተን፤  እስላምና በኢትዮጵያ ምድር ለመስፋፋት አስተዋጽኦ ያደረገው፤ የጠመንጃ መሳሪያ የሙስሊሞቹ መሪ የነበረ በመጀመሪያ በእጁ በቱርክ በኩል ከልዩ ስልጠና ጋር ስለገባ፤ ብዙውን ሰው አሰለመ ወደሚለው ያደርሰናል። እናም፤ ሙስሎሞች ጥፋት ስላጠፉ…..የሚል ጭልጥ ያለ ውንብድና ውስጥ ይከተናል። እኔ ግን ይሄን አልቀበለውም። ምንም ይሁን ምን፤ ደካማ ጎናችንን በመጠቀም፤ የውጭ ሃይሎች የጫኑብን መከራ ነበር ብዬ ነው የማልፈው። ለዛሬ ችግራችንም መጥቀስን አልፈልግም። ምክንያቱም፤ በእነሱ ተንኮል ስር እንደገባሁ ስለምቆጠርው። እናም ጁዋር፤ የኦሮሞ ችግር በውኑ በአማራው የደረሰብት መከራ ነበርን ለማት ታሪኩን፤ መሳሪያ ከመግባቱ በፊት የነበረውን ሁኔታ በጥልቅ እንዲያነቡና ለሁላችን የሚያስማማ፤ እያንዳንዱ ዜጋ የተከበረባት ኢትዮጵያን ለማዬት እጅግ ወሳኝ ነው እላለሁ።
አበቃሁ።

Human right South Ethiopia Documentary film Ethiopia


ኢትዮጵያዊቷ ወጣት በአትላንታ 25 ዓመት እስር ተፈረደባት

ኢትዮጵያዊቷ ወጣት ሮዳስ ተክሉ እዚህ አትላንታ ከተማ በዋለው የወንጀል ጉዳዮች ችሎት ቀርባ ጉዳይዋ ሲታይ ከቆየ በኋላ ባለፍው ሰኞ MAY 20/2013 ….. 25 ዓመት እስር ተፈረደባት። ሮዳስ ተክሉ ይህ የተፈረደባት የሰው ነፍስ በማጥፋቷ ወንጀሉንም መፈጸሟን በማመኗ ነው።
የኋላ ታሪኩ እንዲህ ነው። ፌብሩዋሪ 5 ቀን 2009 አመሻሽ ላይ በአትላንታ የተፈጸመው ወንጀል መላው የአትላንታ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን በቅርብ፣ ነገሩን የሰሙና በሌሎች ከተሞች ያሉትን ደግሞ በሩቅ ያስደነገጠ ነበር። 3754 ቢፈርድ ሃይዌይ የሚባለው የአትላንታ መንገድ ላይ የጸጉር መከርከሚያ ሱቅ ከፍቶ በመስራት ላይ የነበረው ኤርሚያስ አወቀ ፣ ማምሻውን ጭምር አምሽቶ እየሰራ ነበር። ከምሽቱ 8 ፒ ኤም አካባቢ ሮዳስ ተክሉ ሱቁ ድረስ መጣች።
የፖሊስ ሪፖርት እንደሚያሳየው ሮዳስ ሱቁ ድረስ ከመጣች በኋላ ጭቅጭቅ ተጀመረ። እሱ እንድትወጣለት ቢጠይቃትም አልወጣችም። ይልቁኑ በእጇ ሽጉጥ ይዛ ስለነበር ፣ ስልኩን አንስቶ 911 ደወለ፣ ስልኩን ላነሳችው ኦፕሬተር “አንዲት ሴት ሱቄ ድረስ መጥታ ልትገለኝ እያስፈራራችኝ ነው፣ መሳሪያ ይዛለች .. እያለ ገና ተናግሮ ሳይጨርስ ስልኩ ተቋረጠ። ከዚያ በኋላ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች የጥይት ድምጽ መስማታቸውን ይናገራሉ።
ፖሊስ ካለበት፣ ነገሩን የሰሙም በጸጉር ቤቱ አካባቢ ሲደርሱ ኤርሚያስ በደም ተነክሮ ወድቋል፣ ወዲያው ወደ ሆስፒታል ተወሰደ ፣ ሆስፒታል ሲደርስም ህይወቱ አለፈ። በወቅቱ አንዲት ሴት ከቤቱ ወጥታ ስትሄድ አይተናል ከሚል ጥቆማ ውጪ ማን ገደለው የሚለው ጥያቄ እንቆቅልሽ ሆነ።
በማግስቱ ፌብሩዋሪ 6 ግን ፖሊስ ሮዳስ ተክሉ የተባለችና የቀድሞ ፍቅረኛው ነች የተባለች ሴት በጥርጣሬ መያዙን አስታወቀ። እሷም ወደ እስር ቤት ተወሰደች። ኤርሚያስም የፖሊስ ምርመራ ከታወቀና ዶክተሮች የሞቱን መንስኤ ካስታወቁ በኋላ ፌብሩዋሪ 11 ቀን በርካታ የአትላንታ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በጸጉር ቤቱ ደጃፍ የሻማ ማብራት ሰነ ስር ዓት ተካሄደ፣ በማግስቱ ፌብሩዋሪ 12 ጸሎተ ፍትሃት ከተደረገለት በኋላ አገር ቤት ተወስዶ እንዲቀበር በተያዘለት ፕሮግራም ይሄዳል ሲባል ፣ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ ያስፈልገኛል በማለቱ እስከ ፌብሩዋሪ 24 ሳይላክ ቆየ። ፌብሩዋሪ 24 ቀን ግን አስክሬኑ ወደ አገር ቤት ለቀብር ተላከ።
ከዚያ በኋላ ዜናው በአድማስ ሬዲዮም ሆነ አትላንታ ባለው ድንቅ መጽሔት ከወጣ በኋላ በወቅቱ የወጣት ሮዳስ ተክሉ ቤተሰቦች “እሷ በግድያው የለችበትም፣ ይህንን ድርጊት እሷ ትፈጽማለች ብሎ ማሰብ ትክክል አይደለም” ሲሉ ተናግረው ነበር። ሆነም ቀረ ላለፉት አራት ዓመታት ነገሩ ከፍርድ ቤት እስር ቤት ፣ ከ እስር ቤት ፍርድ ቤት ሲንከባለል ቆየ፣ የ ኤርሚያስ አወቀ የቅርብ ቤተሰብ የሆኑት አቶ ላቀው ለአድማስ ሬዲዮ እንደገለጹት በመካከል ተጠርጣሪዋ ልጅ፣ በጠበቆቿ አማካኝነት “አእምሮዋ ትክክል አይደለምና ለፍርድ ልትቀርብ አይገባም” ብለው ሲከራከሩ የቆዩ ሲሆን፣ ዳኞቹም የ አ ዕምሮዋ ነገር በሃኪሞች እንዲታይ ፈቅደው ቆይተዋል። በኋላ ግን ችሎት መቆም እንደምትችል በመታመኑ ፣ ጉዳዩ በከሳሽ አቃቤ ህግ እና በተከሳሽ ሮዳስ ተክሉ ጠበቆች መካከል ክርክሩ ቀጥሎ አራት ዓመት ከፈጀ። እንደ አቶ ላቀው ገለጻ ፣ በመጨረሻ ላይ ሮዳስ ወንጀሉን መፈጸሟን እንድታምን ተጠይቃ “አዎ ፈጽሜያለሁ፣ ነገር ግን በደም ፍላትና ሳላስበው ያደረኩት ነው” ስትል በማመኗ ዳኛዋ 25 ዓመት ጽኑ እስራት ፈርደውባታል። ምናልባት ጥፋቷን ባታምን እና ነገሩ በክርክሩ ብትሸነፍ የሞት ፍርድ ሊጠብቃት ይችልም ነበር ብለዋል።
ዳኛዋ በፍርድ ውሳኔያቸው እንደገለጹት “ ኤርሚያስ ገበየሁን በ 10 ጥይት መግደል ሳይታሰብ፣ ባጋጣሚ የተደረገ አይደለም” ሲሉ ውሳኔያቸውን አጽንተዋል።
በተያያዘ ሁኔታ ሮዳስ ተክሉ እዚያው እስር ቤት እያለች አንዲት ሴት ልጅ መውለዷም ታውቋል። የወለደችው ግሬዲ ሆስፒታል በፖሊስ ታጅባ ሄዳ ሲሆን፣ ባሁኑ ሰአት ህጻኗን አንዲት ነርስ እዚያው ግሬዲ እያሳደገቻት መሆኑ ሲታወቅ፣ የህጻኗን አባት በተመለከተ ዳኛዋ “የቀረበልኝ የዲ ኤን ኤ ምርመራ ስለሌለ፣ በልጅቷ አባት ጉዳይ የምሰጠው አስተያየት የለም” ሲሉ መናገራቸውም ታውቋል። 
(ምንጭ አድማስ ሬዲዮ አትላንታ)zehabesha.com

Thursday, May 16, 2013

በረከት በቀለ (ፍልፍሉ) ጨምሮ 12 ኮሜዲያኖች ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነው ።

May 15, 2013
 
እያንጓለለ በሚለው አዲሱ የኮሜዲ(ቀልድ)ስራቸው ክስ የተመሰረተባቸው 13 ኮሜዲያን በመጭው ማክሰኞ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ።አሳቡዮገዳ የሚባል የእምነት ተቋም ውስጥ ክስ የተመሰረተባቸው በረከት በቀለ (ፍልፍሉ) ተመስገን ተመላኩ ፣ጥላሁን እልፍነህ ፣ዋነሶች ፣ሙሉ ቀን ተሾመ (የቴዎድሮስ ተሾመ ታናሽ ወንድም)እና ሌሎችም የሚገኙበት ክስ ነው ።ኮሜዲያኑ የተከሰሱት እያንጓለለ በሚለው አዲስ የፊልም አልበማቸው ላይ የአሳቡዩገዳ የእምነት ተቋምን የዝሙት ማካሄጃ አስመስለው አቅርበዋል በሚል እና የእምነት ተቋሙ አምልኮቱ ይጠቀምባቸዋል የሚላቸውን ስኒ ፣ጀበና፣ ማጨሻ በሚያጣጥል እና በሚያናንቅ መልኩ ተጠቅመውበታል በሚል ነው ክሱ የተመሰረተው።
ኮሜዲያኖቹ የፍርድቤት መጥሪያ የደረሳቸው ሲሆን የፊታችን ማክሰኞ ፍርድቤት ቀርበው ክሱ ጉዳያቸውን የሚታይበትን ሂደን ለመከታተል ነው።በዚህ በጉዳዩ ዙሪያ ያናገርነው እና በሰሜን አሜሪካ ለተወሰነ ጊዜያት ኑሮውን ያደረገው በረከት በቀለ ፍልፍሉ እንደገለጸው ከሆነ የክሱ ሂደትም ሆነ ሁኔታው እሱን እና ጓደኞቹን ያስገረመ ከመሆኑም በላይ ለጉዳዩ ምንም ጥልቀት እውቀት እንደሌለው እና የቀልድ ስራውን ሰርቶ ከሃገር ለስራ ግዳይ መውጣቱን ለማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል በስልክ ባደረገው መግለጫ ተናግሮአል። እኛ የማንኛውንም የእምነት ተቋም አንነቅፍም ነገር ግን መቀለድ ማለት ሆኖ መገኘት አይደለም እና ህረተሰብን ለማስደሰት እና ለማዝናናት ስንል የምንሰራቸው ቁምነገር እና ፌዞች ከክፉ ነገር ጋር ተያይዘው ሊቀርቡ የሚታዩ ሊሆን አይገባም ሲል ጠቅሶአል::filfilu_obama
አንዳንድ የአነጋገርናቸው ሰዎች እንደሚሉት ከሆነ የሃይማኖቱ ተቋሙ ካነሳቸው የክስ ነጥቦች አንዱ ስኒ እና ጀበና ያሉት እቃዎች በሙሉ የአንድ ሃይማኖት መለያ ሳይሆን ማናቸውም የሃገሪቱ ህብረተሰቦች የሚጠቀሙበት ከመሆኑም በላይ አንቋሸውብኛል ማለቱ ተገቢ አለመሆኑን ጠቁመዋ። በሌላም በኩል ያነጋገርናቸው ግለሰቦች ኮሜዲያኖቹ እንዴት ሊከሰሱ ይገባል ሊከሰስ የሚገባው ከሆነ የዚህ ፊልም ስክሪፕት ደራሲ እና አዘጋጅ ብቻ መሆን አለበት እንጂ ደራሲያኖቹ ጨዋታውን ተጫወቱት እንጂ የጭብጡን ሂደት እነርሱ አልመሰረቱትም ሆኖም ግን የተከናወነው የፊልም ሂደት ከጠንቋዩ የአቶ ታምራት ገለታ ጋር የሚያያዝ እና ወቅቱን ጠብቆ የተከናወነ ስለሆነ ክሱ ውድቅ ሊደረግ ይገባዋል ሲሉ የህግ ባለሙያዎች ጠቁመዋል።
ይህንን ሲሉ አንድ ጋዜጠኛ በአዘጋጁ በኩል ክሱ ይቀርብበታል እንጂ በተናጠል ክስ እንደማይቀርብበት የሃገሪቱ ህግ ይጠቅሳል በተመሳሳይ መልኩ የኮሜዲያንም ሆነ ቴአትር በዚህ መልኩ ተያያዥነት ያለው ክስ መሆኑን ሊታወቅ እና ኮሜዲያኑ ነጻ ሊሆኑ ይገባል በማለት አክለዋል።በማንኛውም አለም ኮሜዲያኖች በሚያውት እና በሚሰሙት አዳዲስ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በመቀለድ ህብረተሰብን ቁምነገር ለማስጨበጥ የሚጥሩ የስራው ባለሙያዎች መሆናቸውን መዘንጋት የለብንም ።በዚህ ጉዳይ ላይ በኢትዮያ የሚገኘውን የኮሜዲያን ማህበር አባል እና አስተዳዳርን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም
 ማለዳ ታይምስ

Tuesday, May 14, 2013

ብአዴን እየተበጠረ ነው ሴኮ ቱሬ ተነሱ ተባለ


Image
ብአዴን እየተበጠረ ነው ሴኮ ቱሬ ተነሱ ተባለ
የኢህአዴግ የረዥም ጊዜ የውጭ ግንኙነት ሃላፊ በመሆን እያገለገሉ ያሉት ሴኮ ቱሬ ጌታቸው ከሃላፊነታቸው መነሳታቸው ተሰማ። ጉዳዩ ከሙስና ጋር በተያያዘ ስለመሆኑ በግልጽ የታወቀ ነገር የለም። የአቶ ሴኮ ከሃላፊነት መባረር ማረጋገጫ ይሰጥበታል ተብሎ ይጠበቃል። አቶ ሴኮ መባረር ብአዴን ላይ የተጀመረ ዘመቻ እንዳለ አመላካች ሲሆን ከግንቦት 1 ጀምሮ አራት ከፍተኛ የብአዴን ሰዎች ከስልጣን መነሳታቸውን ያመላከተ ሆኗል። ውሳኔው በፓርቲው ውስጥ ተፈጥሮ የነበረውን ልዩነት በአሸናፊነት የደመደመው ቡድን የማጥራት ስራውን እያቀላጠፈ ስለመሆኑ አመላካች ነው እየተባለ ነው። ኢህአዴግ ግን ለጀመረው የጸረ ሙስና ትግል ” የህዝብ ድጋፍ” እየጠየቀ ነው። ሴኮ ቱሬን አስመልክቶ ኢህአዴግ ለጊዜው በይፋ የሰጠው መግለጫ የለም

17 ሰዎችን የገደለው የፌደራል ፖሊስ ማንነት በውል አልታወቀም


ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-እሁድ ግንቦት4፣ 2005 ዓም ከምሽቱ 2 ሰአት ከ45 ደቂቃ ላይ ፣ የሁለት አመት ህጻንን ጨምሮ 17 ሰዎችን በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 11 ወይም በተለምዶ አባይ ማዶ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በግፍ የገደለው የፌደራል ፖሊስ አባል ማንነት እና የገደለበት ምክንያት በውል አለመታወቁን ተከትሎ የተለያዩ መላምቶች እየተሰነዘሩ ነው።

ወታደሩ ድርጊቱን የፈጸመው አንድ ያፈቀራት ወጣት ከእርሱ ጋር ለመቀጠል ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነው የሚል አስተያየቶች ቢሰሙም በሌላ በኩል ደግሞ ግለሰቡ የሌላ ብሄር ተወላጅ በመሆኑ ጥላቸውን ለመግለጽ በሚል የፈጸመው ነው የሚሉ ወገኖች አሉ።

እሁድ ምሽት ወታደሩ ወደ አፈቀራት ልጅ ቤት ቢሄድም እናቷን ብቻ በማግኘቱ ተኩሶ የልጂቱን እናት ተኩሶ መግደሉን ከዚያ በሁዋላ መንገድ ላይ ያገኛቸውን ሁሉ መግደል መጀመሩን አንዳንድ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ግን ግለሰቡ ከፍተኛ ወታደራዊ ጥበቃ በሚደረግበት የብአዴን ጽህፈት ቤት እና የሰማእታት ሀውልት በሚገኙበት አካባቢ አካባቢ መሆኑ እና ሌሎች ፖሊሶችም አፋጣኝ እርምጃ ለመውሰድ አለመቻላቸው ፣ ከዚህም በተጨማሪ ገዳዩ ወታደር የሌላ ብሄር ተወላጅ ነው የሚለው ወሬ በስፋት መሰራጨት አብዛኞቹ ወጣቶች ጉዳዩ ከፖለቲካ ከፖለቲካ ጋር የተያያዘ ነው በማለት አስተያየት እንደሚሰጡ የባህርዳር ዘጋቢያችን ገልጿል።

የባህር ዳር ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር ደረጀ አቻምየለህ የገዢው ፓርቲ ልሳን ለሆነው ራዲዮ ፋና ” ግለሰቡ በውል ባልታወቀ ምክንያት በመንገድ ላይ በከፈተው ተኩስ 12 ሰዎች መገደላቸውን በሰዓቱም ወታደሩን በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ ክትትል ሲያደርግ እንደነበርና በመጨረሻም ራሱን በወንዝ ውስጥ በመወርወር ህይወቱን እንዳጠፋ” ተናግረ= ዋል።

የፖሊስ አዛዡ “ድርጊቱን የፈፀመው ግለሰብ የፖሊስ አባል መሆኑን ገልጸው ፥ ድርጊቱን የፈፀመበት ምክንያትም ግለሰባዊ ” ነው ብለዋል።

ኢህአዴግ ድርጊቱ ከፖለቲካ ጋር የተያያዘ አለመሆኑን ለማስረዳት በከተማው ውስጥ የሚገኙ ዋና ዋና አባሎቹን በማሰማራት ከፍተኛ ቅስቀሳ እያደረገ ነው።

ይሁን እንጅ መንግስት የሟቾቹን ቁጥር 12 አድርጎ ማቅረቡ ህዝቡን ለባሰ ጥርጣሬ እንደከተተው ዘጋቢያችን ገልጿል። በርካታ የአይን እማኞች እንደሚሉት የሟቾች ቁጥር 17 ደርሷል። መንግስት ወታደሩ ራሱን እንዳጠፋ አድርጎ ቢገልጽም፣ ነዋሪዎች ግን ወታደሩ ራሱን ቢያጠፋ ኖሮ አስከሬኑ ይገኝ እንደነበር፣ በተለይም ደግሞ አባይ በአሁኑ ሰአት ከመቼውም ጊዜ በላይ ቀንሶ የሚታይበት ጊዜ በመሆኑ ወታደሩ ራሱን ወደ ውሀው ቢወረውር እንኳ የመትረፍ እድል ሊኖረው እንደሚችል በመግለጽ በመንግስትን በኩል የቀረበውን ዘገባ አልተቀበሉትም።

ከተገደሉት መካከልም አንድ የሁለት አመት ተኩል ህጻን እና ሴቶች ይገኙበታል። የ7ቱ የቀብር ስነስርአት ዛሬ በደብረ አባይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የክልሉ ፕሬዚዳንት አያሌው ጎበዜ በተገኙበት ተፈጽሟል።

ከወራት በፊት ኮሶበር በምትባል ከተማ አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል በርካታ ሰዎችን መግደሉን መዘገባችን ይታወሳል። የፌደራል ፖሊስ አባላት በየጊዜው በህዝቡ ላይ የሚፈጽሙት በደል እየጨመረ ቢመጣም በመንግስት በኩል እርምጃዎች ሲወሰዱ አይታይም።
ESAT
17 ሰዎችን የገደለው የፌደራል ፖሊስ ማንነት በውል አልታወቀም
ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-እሁድ ግንቦት4፣ 2005 ዓም ከምሽቱ 2 ሰአት ከ45 ደቂቃ ላይ ፣ የሁለት አመት ህጻንን ጨምሮ 17 ሰዎችን  በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 11 ወይም በተለምዶ አባይ ማዶ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በግፍ የገደለው የፌደራል ፖሊስ አባል ማንነት እና የገደለበት ምክንያት በውል አለመታወቁን ተከትሎ የተለያዩ መላምቶች እየተሰነዘሩ ነው።

ወታደሩ ድርጊቱን የፈጸመው አንድ ያፈቀራት ወጣት ከእርሱ ጋር ለመቀጠል ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነው የሚል አስተያየቶች ቢሰሙም በሌላ በኩል ደግሞ ግለሰቡ የሌላ ብሄር ተወላጅ በመሆኑ ጥላቸውን ለመግለጽ በሚል የፈጸመው ነው የሚሉ ወገኖች አሉ።

እሁድ ምሽት ወታደሩ ወደ አፈቀራት ልጅ ቤት ቢሄድም  እናቷን ብቻ በማግኘቱ ተኩሶ የልጂቱን እናት ተኩሶ መግደሉን ከዚያ በሁዋላ መንገድ ላይ ያገኛቸውን ሁሉ መግደል መጀመሩን አንዳንድ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ግን ግለሰቡ ከፍተኛ ወታደራዊ ጥበቃ በሚደረግበት የብአዴን ጽህፈት ቤት እና የሰማእታት ሀውልት በሚገኙበት አካባቢ አካባቢ መሆኑ እና ሌሎች ፖሊሶችም አፋጣኝ እርምጃ ለመውሰድ አለመቻላቸው ፣ ከዚህም በተጨማሪ ገዳዩ ወታደር የሌላ ብሄር ተወላጅ ነው የሚለው ወሬ በስፋት መሰራጨት አብዛኞቹ  ወጣቶች ጉዳዩ ከፖለቲካ ከፖለቲካ ጋር የተያያዘ ነው በማለት አስተያየት እንደሚሰጡ የባህርዳር ዘጋቢያችን ገልጿል።

የባህር ዳር ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር ደረጀ አቻምየለህ የገዢው ፓርቲ ልሳን ለሆነው ራዲዮ ፋና  ” ግለሰቡ በውል ባልታወቀ ምክንያት በመንገድ ላይ በከፈተው ተኩስ 12 ሰዎች መገደላቸውን በሰዓቱም ወታደሩን በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ ክትትል ሲያደርግ እንደነበርና በመጨረሻም ራሱን በወንዝ ውስጥ በመወርወር ህይወቱን እንዳጠፋ” ተናግረ= ዋል።

የፖሊስ አዛዡ “ድርጊቱን የፈፀመው ግለሰብ የፖሊስ አባል መሆኑን ገልጸው ፥ ድርጊቱን የፈፀመበት ምክንያትም ግለሰባዊ ” ነው ብለዋል።

ኢህአዴግ ድርጊቱ ከፖለቲካ ጋር የተያያዘ አለመሆኑን ለማስረዳት በከተማው ውስጥ የሚገኙ ዋና ዋና አባሎቹን በማሰማራት ከፍተኛ ቅስቀሳ እያደረገ ነው።

ይሁን እንጅ  መንግስት የሟቾቹን ቁጥር 12 አድርጎ ማቅረቡ ህዝቡን ለባሰ ጥርጣሬ እንደከተተው ዘጋቢያችን ገልጿል። በርካታ የአይን እማኞች እንደሚሉት የሟቾች ቁጥር 17 ደርሷል። መንግስት ወታደሩ ራሱን እንዳጠፋ አድርጎ ቢገልጽም፣ ነዋሪዎች ግን ወታደሩ ራሱን ቢያጠፋ ኖሮ አስከሬኑ ይገኝ እንደነበር፣ በተለይም ደግሞ አባይ በአሁኑ ሰአት ከመቼውም ጊዜ በላይ ቀንሶ የሚታይበት ጊዜ በመሆኑ ወታደሩ ራሱን ወደ ውሀው ቢወረውር እንኳ የመትረፍ እድል ሊኖረው እንደሚችል በመግለጽ በመንግስትን በኩል የቀረበውን ዘገባ አልተቀበሉትም።

ከተገደሉት መካከልም አንድ የሁለት አመት ተኩል ህጻን እና ሴቶች ይገኙበታል። የ7ቱ የቀብር ስነስርአት ዛሬ በደብረ አባይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የክልሉ ፕሬዚዳንት አያሌው ጎበዜ በተገኙበት ተፈጽሟል።

ከወራት በፊት ኮሶበር በምትባል ከተማ አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል በርካታ ሰዎችን መግደሉን መዘገባችን ይታወሳል። የፌደራል ፖሊስ አባላት በየጊዜው በህዝቡ ላይ የሚፈጽሙት በደል እየጨመረ ቢመጣም በመንግስት በኩል እርምጃዎች ሲወሰዱ አይታይም።

! ….. ኢህኣዴግና ሙስና ………!

ኢህኣዴግ የተገነባው በሙስና ነው። የፓርቲው ሰዎች የተሰባሰቡበት ነጥብ የፖለቲካ ዓላማ ሳይሆን እህል- ዉሃ ነው። ወደ ፓርቲው በመቀላቀላቸው እህል-ዉሃውን ካገኙት (የፓርቲው አባላት ያልሆኑ ካላገኙት) የሚያገኙትን ነገር በሙስና መሆኑ ነው። አዎ! “ሙስና” ሰዎች ወደ ፓርቲው የሚገቡበት መንገድ ያመቻቻል። በመጨረሻ ደግሞ ለፓርቲው ህልውና አደጋ ይሆናል። ኢህኣዴግ በሙስና (በጥቅም በመደለል) ብዙ … አባላት አፍርቷል። እነዚህ አባላት ለፓርቲው አደጋ እየፈጠሩ ነው። በዚህ መሰረት ገዢው ፓርቲ መስቀለኛ መንገድ ቆሟል። ፓርቲው በስልጣን መቆየት ይፈልጋል። በስልጣን ለመቆየት ግን ልማት ማምጣት ያስፈልጋል። ልማት ለማምጣት ሙስና ማስወገድ ወይ መቀነስ ግድ ይላል። ሙስና ከተቀነሰ አባላት ይቀነሳሉ (በሙስና የሚበላ ነገር ካላሳየሃቸው አባላት እንዲሆኑና ሁነው እንዲቆዩ በምን ታጠምዳቸዋለህ???)። አባላት ከተቀነሱ ፓርቲው ይዳከማል። በሙስና የተገነባ ድርጅት ረዥም ዕድሜ ሊኖረው አይችልም። ለዚህ ነው ኢህኣዴጎች በሙስና ጉዳይ አይተው እንዳላዩ የሚሆኑት። ስለዚህ ኢህኣዴግ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነው። በኢህኣዴግ ብዙ የሙስና ተግባራት እንደሚከናወኑ ይታወቃል። እህል-ዉሃ ያሰባሰባቸው ግብዝ አባላት ገዢው ድርጅት ብዙ ዕድሜ ሊኖረው እንደማይችል ሲረዱ የመንግስት ሃብት ዘርፈው ለማምለጥ ጥረት ማድረጋቸው አይቀርም። (በደርግ ግዜም ተመሳሳይ ነገር ተፈፅሞ ነበር)። በሌላ በኩል ደግሞ እርስበርሳቸው መግባባት ሲያቅታቸው አንዱ ሌላውን ለማሸነፍ (ወይ ለማባረር) አሸናፊውን ለተሸናፊው ማሳሰር ይችላል። (ድሮ በአብዮቱ ግዜ ‘ምስጢር እንዳያወጡ’ በሚል ሰበብ ይገደሉ ነበር)። ለማሳሰር ምክንያት ስለሚያስፈልግ በኢህኣዴጋዊ ስልት “ሙስና” ጥሩ መሳርያ ነች። ምክንያቱም በኢህኣዴግ መንግስት ሙስና ያልነካው ባለስልጣን አለ ለማለት ይከብዳል። የሆነ ሁኖ ኢህኣዴጎች (በሙስና ምክንያት ይሁን በሌላ) ጓዶቻቸውን ማሳሰር ጀምረዋል። ግን እነ መላኩ ፋንታ በሙስና ከታሰሩ እነ አስመላሽ ወልደስላሴስ በምንድነው የሚታሙ? ብቻ እርስበርሳቸው መወነጃጀል ከጀመሩ በፓርቲው ውስጥ ያለ ችግር ሊፈነዳ ተቃርቧል ማለት ነው። በሙስና ሰበብ ማሳሰር ከጀመሩ ሁሉም ሙስና የሰሩ ባለስልጣናት መታሰር አለባቸው ማለት ነው። ሁሉንም ከታሰሩ፤ አሳሪዎቹም ጭምር ይታሰራሉ (ምክንያቱም ኣሳሪዎቹም ከሙስና የፀዱ አይደሉም)። ሁሉም አባላት ከታሰሩ ኢህኣዴግ ታሰረ ማለት ነው። ኢህኣዴግ ከታሰረ እኛ ነፃ ወጣን ማለት ነው። ያኔ ከኢህኣዴጎች በምን እንደምንሻል እናሳያለን። ስለዚ በሙስና ምክንያት ማሰር መጀመራቸው መልካም ነው። ችግሩ ግን የሙስና ወንጀል አሳሪዎቹ ጋር ሲደርስ ያስቁሙታል። ሙሰኞቹ ይታሰራሉ፤ ሙስኞቹ ያስራሉ። ሙስኞቹ ሄደው ሙሰኞቹ ይመጣሉ። ለውጥ የለውም። ከ“ባለ ራእዩ መሪ” ሞት በኋላ በትግራይ ክልል ሙስና “ሕጋዊ ስራ” የሆነ ይመስላል፣ የተለመደ ተግባር ነው። ሙሰኞቹ የመንግስት ሃብት መዝብረው ሲያበቁ ሌላ ተጨማሪ ውድመትም ያደርሳሉ። መቀለ ውስጥ ነው። ከሦስት ዓመታት በፊት በአንድ የዓይን ሕክምና ክሊኒክ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ይደርሳል። በዛ ግዜ መንስኤው አልታወቀም። በኋላ ሲጣራ ግን እሳቱ የለኮሱት የክሊንኩ ሰራተኞች ሁነው ተገኙ። ለምን ቢባል፣ ሰዎቹ የክሊኒኩ ገንዘብ ዘርፈውታል። የኦዲቲንግ ግዜ ስለደረሰ የዘረፉትን ገንዘብ እንዳይታወቅ (ገንዘብ የተቀመጠበት ክፍል ማውደም) በእሳት ማጋየት ብቸኛው አማራጭ ሁኖ አገኙት። በቅርቡም በሑመራ ከተማ በተመሳሳይ ምክንያትና አደጋ አንድ ሆስፒታል ወድሟል። በዚሁ ወር ውስጥም በነበለት ከተማ አንድ ትምህርትቤት በእሳት ቃጠሎ መውደሙ ይታወቃል። ማን እንዳቃጠለው፣ በምን ምክንያት እንደተቃጠለ እስካሁን አይታወቅም። ምናልባት በሙስና ይሆን እንዴ? ግን መላው አካላቱ ሙስና የሆነ ድርጅት እንዴት ሙስና ሊዋጋ ይችላል? ለኢህኣዴግ ‘ሙስናን መዋጋት’ ማለት ኢህኣዴግ ራሱን መዋጋት ማለት ነው። ይሄ ደግሞ ራስ ማጥፋት ነው። እስቲ ኢህኣዴግ ራሱ በራሱ ሲያጠፋ እንይ!?


 በአብረሃ ደስታ