በጥያቄ ምልክትና እና በቃለ አጋኖ የታጀበውን ‘’ይልቃል አዲሱ ልደቱ” በሚል ርዕስ ወጣት ዳዊት ስለሞን በብዕር ስም /አይናለም/ የተፃፈውን ባለ ብዙ ሀሳብ ፅሁፍ አነበብኩት ፡፡ አንድ ፅሁፍ ሲፃፍ አንባቢ ሊታዘብ ይችላል ሰለዚህ እውነት ላይ እና እየታዩ ካሉ ነባራዊ ሁኔታዎች አንፃር መቃኘት አለበት የሚለው ዋና ጉዳይ በዚህ ፀሁፍ ውስጥ ለኔ አልታየኝም ፡፡ በፅሁፉ ውስጥ አንባቢን ለማሳመን የተደረጉ ውጣ ውረዶች ከመጥቀሴ በፊት ፀሀፊው አባል በሆነበት አንድነት ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ ውስጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተመለከትኩትን የሚበረታታ ጉዳይ ከማሳሰቢያው እጠቅሳለሁ፡፡
ማሳሰቢያ ‘’ይልቃል አዲሱ ልደቱ” ፅሁፍ ፀሀፊ ዳዊት ሰለሞን የአንድነት ፓርቲ ልሳን የሆነው ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ኣዘጋጅ ለመሆኑ አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የአንድነት አባል ስለነገረኝ ከዚህ በታች የምጠቀመው የብእር ስሙን ሳይሆን ዳዊት የሚለውን ዋና ስሙን መሆኑን አሳውቃለሁ፡፡
መኢአድ ሲባል ኢ/ር ሀይሉ ሻወል፣ ደቡብ ህብረት ሲባል ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ፣ ኦብኮ ሲጠቀስ ዶ/ር መረራ ጉዲና… የፖለቲካ ተክለ ሰውነት ለብሰው ብቅ ይሉብናል፡፡ ይህ የፖለቲካ ተክለ ሰውነት በአንድት ውስጥም ግዝፈቱን ሳይቀንስ ተንሰራፍቶበት ቆይቷል፡፡ ይህ ማለትም አንድነት ሲባል በየደቂቃው የሚለዋወጥ አቋም ያለው ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው እና ባለመልካም ባህሪው ዶ/ር ሀይሉ አርአያ ድቅን ይሉብን ነበር እነአቶ አስራት ጣሴን አስከትለው፡፡ ወጣት ዳዊትም በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ የሚታዩ ችግሮች ብለው ከጠቀሱዋቸው መካከል የግለሰብ ተክለ ሰውነት መገንባት አንዱ ነው፡፡
እኔም የግለሰብን ተክለ ሰውነት አንዱ መስፈርት አድርጌ ፓርቲዎችን ስገመግም አንድነት አሁን ካሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ውስጥ የተሻለ ነው እንድል ያደረገኝ ከግለሰብ ትከሻ ላይ ወርዶ አበረታች የሚባል የቡድን ስራ ማክናውን ላይ በመሆኑ ነው፡፡
የተመለከትኩትን ጠንካራ ጎን ከገለፅኩ በኋላ የፓርቲው አባል የሆኑት ወጣት ዳዊት ፅሁፍ ላይ ላተኩር፡፡ ሀሳብን በነፃነት ለመግለፅ ያደረገውን ጥረት በማድነቅ ፅሁፉ መጀመሪያ ላይ የጠቀሱት የደርግ/ የኢህአፓ /የመኢሶን ፖለቲካዊ መጠላለፍ ዛሬ ላይ እንዲመጣ ወይም ዛሬ ላይ ያለው የመፈራረጅ ፖለቲካ እንዲቀጥል ታጥቀው የተነሱ ነው የሚመስለው፡፡ እንዴት! ማለት ጥሩ….. በአዲስ መስመር ከመቀጠሌ በፊት እኔ የሰማያዊ ፖርቲ አባልም ደጋፊም አለመሆኔ ሊታወቅ ይገባል፡፡
አንባቢን ለማሳመን እና ሰማያዊ ፓርቲ የወጣቶች ስብስብ መሆኑን ለማጣጣል የአቶ ልደቱ ወጣት መሆን በመጥቀሥ በጥሩ ሁኔታ እየተቀሰቀሰ ያለውን ፖለቲካ ለመጥለፍ ‹‹አዲሶቹ ጎጆ ወጪዎች ከመጀመሪያው ቤታቸው ሲወጡ በአብዛኛው ባዶ እጃቸውን አይሆኑም፣የእናት ፓርቲያቸውን የፖለቲካ ፕሮግራም፣አደረጃጀትና አባል ይዘው ሹልክ ይላሉ፡፡ለዚህ እንደምሳሌ ኢዴፓና ሰማያዊ ፓርቲን መውሰድ ይቻላል፡፡›› ይሞክራሉ፡፡ እኔም አንድ የመጥለፉ መንገድ ልከተልና ፀሀፊውን ልጠይቀው፡፡ ቅንጅት የአራት ፓርቲዎች ጥምረት ነው፡፡ መሪዎቹ ታስረው ሲፈቱ በጋራ መቆም አቃታቸውና የየራሳቸውን ደጋፊና አባል በመያዝ ለአራት ተሰነጣጠቁ፡፡ከግንቦት 7 በስተቀር ሁሉም የሰላማዊ ትግል መርጦ የቅንጅቱን መንፈስና ፕሮግራም ለማስቀጠል በያለበት ይንቀሳቀሳል፡፡ ከነዚህ ውስጥም አንድነት አንዱ በመሆኑ የእናት ድርጀቱን አባል ፕሮግራም ይዞ ሹልክ አለ ማለት ነው ወይስ አንድነት የተለየ ፕሮግራም አረቀቀ? ይህን ለመመለስ የቅንጅትንም የአንድነት በደንብ ፕሮግራሞች ማየት ያስፈልጋል እንዳትረሳው!
የሰማዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር ላይ ያስቀመጠው ቅሬታ / ግን ሰይጣናዊ ቅናት ብለው በትክክል ይገልፀዋል/ ጠቅለል አርጌ ለመግለፀ በሁለት መክፈል እፈልጋለሁ፡፡ ሊቀመንበሩ ላይ የቀረበው ቅሬታ ለፖለቲካው በማሰብ በሚል እና ፀሀፊው ጎልቶ ለመውጣት ባለው ጉጉት የሚከተላቸው መንገዶች በሚሉ ፡፡
ለፖለቲካው በማሰብ
ኢ/ር ይልቃል /የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር/ “ፓርቲዎች አሉ ብለን አናምንም ተባበሩ የምትለን ከማን ጋር ነው ? መድረክ ምን ሰራ አንድነትና መድረክ እየተባሉ አይደለም? አንድነት ውስጥ የገባው ብርሃን ወጥቷል እኛ ከማን ጋር እንተባበር ? ብለዋል ብሎ ወጣት ዳዊት ይኮንናል፡፡ የኢ/ር ይልቃል ንግግር ላይ ያለውን ስህተት ለማሳየት ፓርቲዎቹ የሰሩትን ምንም መረጃ ማቅረብ ስላልቻለ በደፈናው በህብረት ለመስራት አንፈልግም ብለዋል ሲል ተንከባሎ ያልፋል፡፡ የመድረክ አባል ፓርቲዎች የደቡብ ህብረት ከፕ/ር በየነ ሳምሶናት ውስጥ መውጣት ሳይችል፣ ኦፍዴን ከአቶ ቡልቻ የግል ንብረትነት ሳያልፍ፣ ኦብኮ ከዶ/ር መራራ የኮሜዲ ምሽት ሳይላቀቅ ፣አረና አባላቱ በነፃ ዝውውር ለሰማያዊ ፓርቲ እየፈረሙ ባሉበት ሰአት እና አንድነት በኣዛውንቶችና በወጣቶች መሀክል በሚደረግ ገመድ ጉተታ ፖለቲካ ውስጥ ነው ያለው ስለዚህ ከማን ጋር በህብረት ይስራ ነው የሚባለው፡፡ በተጨማሪም ብርሀንም ከአንድነት የወጣው ገመድ የጉተታ ውጤት ይዞት የሚመጣው ጦስ አስግቶት ነው፡፡ ታዛቢ ስላለ እውነቱ ይህ መሆኑን መግለፅ ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ የተቀረበው ቅሬታ ለፖለቲካው በማሰብ አደለም ለማለት እደፍራለሁ፡፡
በተጨማሪም አንድነትን ጨምሮ ሁሉም የመድረክ ፓርቲዎች ጥርት ያለ የፖለቲካ ፕሮግራም ስለሌላቸው መስማማት አልቻሉም ፡፡ ይህንን ስል በስሜት አለመሆኑን ለማስገንዘብ ሁለት ምሳሌ ልጥቀስ፡፡ የመሬት ጥያቄና የመገንጠል መብት ፓርቲዎቹ ከግንባርነት እንዳያልፉ ማነቆ ሆነው ስራ እዳይሰሩ ያደረጋቸውን ብቻ ማንሳት በቂ ነው፡፡ ይህም እውነት ሲገለጽ በሰማያዊ ፓርቲ ፕሮግራም ላይ የተቀረበው ቅሬታ ለፖለቲካው በማሰብ አይደለም ለማለት እገደዳለሁ፡፡
ጎልቶ ለመውጣት የሚደረግ ጥረት
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንድነት ከላይ እንደጠቀስኩት ከግለሰብ ስብእና ራሱን በማፅዳት የቡድን ስራን በመጀመር የሚያበረታታ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡ ይህም የቡድን እንቅስቃሴ ባለፉት ግዚያት እንደተመለከትነው በተለያዩ የክልል ከተሞች በመንቀሳቀስ የቀዘቀዘው የህዝብ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ዳግም እንዲያንሰራራ ሚዛን የሚደፋ አስተዋፆ አድረጓል፡፡ ለዚህም አበረታች ጅማሮ ከፊትም ከኋላም በመሆን ከፍተኛ አስተዎ ያደጉትን ግርማ ፣ዳንኤል እና በላይን የመሰሉ ወጣት ፖለቲከኞችን ማመስገን ያስፈልጋል፡፡ በዛውም ልክ ይልቃል ጎልቶ ለመውጣት ይፈልጋል ተብሎ እንደተከሰሰው በአንድነት ህዝባዊ ንቅናቄም ውስጥም በበርካታ ወጣቶች ላይ ጎልቶ የመታየት ፍላጎት ሲከሰት ከርሟል፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዱ ወጣት ዳዊት ይግኝበታል፡፡ እንዴት የሚል ጥያቄ ከተነሳም መልሱን ክዚህ በፊት ወጣቱ የሚያድጋቸውን ጎልቶ ለመውጣት የሚደረግ ድርጊቶች ላሳይ፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አንድነት ፓርቲ ውስጥ የተመለከታቸውን ህፀፆች እንደጋዜጠኝነቱ እንዲታረሙ በበሳል ብእሩ ሲጠቁም የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የጋዜጠኛውን ጥቆማ በመቀበል የታዩትን ችግሮች ለማረም ደፋ ቀና ብለዋል፡፡ ነገር ግን ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ የተባለው ብሂል በወጣቱ ዳዊት ላይ ተተግብሮ ‹‹ ተመስገን ደሳለኝ ሲያዳልጠው›› በሚል ጽኁፍ በአደባባይ ፓርቲውን ለምን ነካ ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት እፍኝ እውቅና ለማግኘት ሲታገል መድከሙ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ ይህ ተግባር በተመስገን ላይ ብቻ የተገደበ እይደለም ፡፡ ብዙ መጥቀስ ይቻላል ነገር ግን ዝም በመባሉ ያሸነፈ ስለመሰለው በተመሣሳይ ላሞኛችሁ አይናችሁን ጨፍሁ ብሎ በኢ/ር ይልቃል ላይ እንዲህ ሲዘምት ጎልቶ ለመውጣት በሚደረግ ጥረት የሚቀዘቅዘው የወጣቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ስላሳሰበኝ ነው ይህን ጽሁፍ ለመጻፍ የተገደድኩት፡፡
በአጠቃለይ የወጣቱ ፅሁፍ ለሀገራችን ፖለቲካ በማሰብ የቀረበ ሀሳብ ሳይሆን ጎልቶ ለመውጣት የሚደረግ ጥረት በመሆኑ የተጀመረው የህዝብን የማንቃት ስራ አዳክሞ ሀገሪቱን በአንባገነንነት ለሚመራው ኢህአዴግ ነው የሚጠቅመው፡፡ ስለዚህ ወጣት ዳዊት ገና ብቅ ብቅ የሚሉ ወጣት ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኛ ተመስገን ላይ በመፃፍ እውቅናን ለማግኘት ከመጣር ከላይ በአንድነት ውስጥ ከባድ እንቅስቃሴ እያደረጉ ያሉትን ምሳሌ በማድረግ ስራቸውን ማጉላት ላይ ብታተኩሩ ወይንም እነሱ ልምድ ካላቸው ፖለቲከኞች ጀርባ ሆነው ልምድ ቀስመው ዛሬ ለሀላፊነት የበቁበትን መንገድ መከተል በሳልነት መሆኑን ሳልጠቁም አላልፍም፡፡ በመጨረሻም ሰማያዊ ፓርቲ አዲስ መስመር…
ምስረታ ጀምሮ አወዛጋቢ የሆነው ሰማያዊ ፓርቲ 8 አመት ሙሉ የቀዘቀዘውን የሀገሪቱ ፖለቲካ ሚዛን በሚደፋ መልኩ ለማሞቅ ( ለማንቀሳቀስ) ጥረት እያደረገ ነው፡፡ ነገር ግን የፓርቲውን አላማና ፕሮግራም እና በፓርቲው ውስጥ ያሉት አመራሮች ከሊቀ መንበር ውጪ ያላቸው የፖለቲካ ብስለት በሰፊው ለህዝብ ስላላደረሰ አውዛጋቢነቱ እንዲቀጥል አድርጎታል ፡፡ ይህም የፓርቲውን አላማና ፕሮግራም እንዲሁም በፓርቲው ውስጥ ያሉት ወጣት አመራሮች ያላቸው የፖለቲካ ብስለት ለሰፊው ህዝብ ካልደረሰ በሀገራችን ለዘመናት ለቆየው የመጠለፍ ፖለቲካ ጭዳ ይሆናል ባይ ነኝ፡፡ በተጨማሪም እንታገልለታለን ለምትሉት ህዝብ የማሳወቅ ፓርቲው ግዴታም አለበት፡፡
Saturday, August 24, 2013
Sport: ሙስሊም ተጨዋችና እግርኳስ
ከሊሊ ሞገስ
እስልምና በምንም አይነት መጠን ቢሆን አልኮልን መጠጣትንም ሆነ ለሌሎች እንዲጠጡ ማበረታትን ይከለክላል፡፡ እናም አምላ ከማሊያው ላይ ምልክቱ እንዲነሳለት ጠይቋል፡፡ አስተዳዳሪውም የስፖርተኛውን ጥያቄ ተቀብለው በጨዋታ ላይ አምላ ማስታወቂያ ያላፈረበትን ማሊያ ለብሶ ተጫውቷል፡፡

(በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 54 ላይ ታትሞ የወጣ)
ፓፒስ ዴምባ ሲሴ ሃይማኖቱን አ ጥባቂ ሙስሊም ነው፡፡ እስልምና ደግሞ ወለድን መብላት ይከለክላል፡፡ የወለድ ስርዓት ያለበት የፋይናንስ አሰራር ውስጥ ተከታዮቹ እጃቸውን እንዳያስገቡ ይደነግጋል፡፡ ኒውካስል ዩናይትድ wonga ከተባለው ኩባንያ ጋር የማሊያ ላይ ስፖንሰርሺፕ ስምምነት መፈራረሙ ለሲሴ አመቺ አልሆነም፡፡ ኩባንያው የአጭር ጊዜ ብድር የሚሰጥና ከፍተኛ ወለድን የሚጠይቅ ኩባንያ ነው፡፡ ኒውካስል ደግሞ የሲሴ ቀጣሪና ደመወዝም ይከፍለዋል፡፡ የሲሴ እምነት ደግሞ ከwonga ጋር ምንም አይነት የስራ ግንኙነት መፍጠርን አይፈቅድም፡፡ በዚህ ላይ በጨዋታዎች ላይ የኩባንያው አርማ የሰፈረበትን ማሊያ ለብሶ የመጫወት ግዴታ አለበት፡፡
የተጨዋቹ ተቃውሞ ከመነሻው ጠንካራ ነበር፡፡ ማሊያውን አልለብስም በሚለው አቋሙ መጽናቱን ለማሳየት ክለቡ ለቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅት ወደ ፖርቹጋል ያደረገው ጉዞ አካል አልሆነም፡፡ ጓደኞቹ ወደ ዝግጅት ሲጓዙ ሲሴ ቀርቶ ከቤተሰቦቹ፣ ከጓደኞቹና ከሃይማኖት ሊቃውንት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ መከረ፡፡
በዚህ መልኩ ተቃውሞን ሲያቀርብ ሲሴ የመጀመሪያው እግርኳስ ተጨዋች አይደለም፡፡ በ2006 ለስፔኑ ሲቪያ በሚጫወትበት ጊዜ ፍሬዲሪክ ካኑቴ 888.com የሚል ፅሑፍ የሰፈረበትን ማሊያ እንደማይለብስ አስታውቋል፡፡ የኢንተርኔት ቁማር ኩባንያ በመሆኑ ነው፡፡ እንደ ሲሴ ሁሉ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆነው ካኑቴ ደግሞ ይህን በማድረግ የመጀመሪው ስፖርተኛ አልነበረም፡፡ ሃሺም አምላ የተሰኘው ደቡብ አፍሪካዊ የክሪኬት ተጨዋች castle lager የተሰኘውን ቢራ ጠማቂ የኩባንያ ዓርማ የሰፈረበትን መለያ ከመልበስ ታቅቧል፡፡
የሲሴ ጥያቄ የአምላ አይነት ተቀባይነት አላገኘም፡፡ ዘግይቶም ማሊያውን ለመልበስ ወስኗል፡፡ ይሁን እንጂ ሲሴ አቋሙን የቀየረበት ምክንያት ዝርዝር አልታወቀም፡፡ ይልቅ ከፖርቹጋል ዝግጅት በቀረበት ሰዓት የብሪታኒያ ጋዜጦች ተጨዋቹ በካዚኖ (የቁማር ማዕከል) ሳለ የሚያሳይ ፎቶግራፍ በአምዶቻቸው ላይ አትመው ነበር፡፡ ፎቶው ሴኔጋላዊው ቁማሩን ሲጫወት ባያሳዩም ከመቆመሪያው ጠረጴዛ አጠገብ (በሚጫወት ሰው ሁኔታ) ተቀምጦ ነበር፡፡ ቁማሩን ተጫውቶ ከሆነ ማሊያውን ላለማድረግ የነበረው አቋም ከልብ አይደለም የሚሉ አስተያየቶች ተሰንዝረውበታል፡፡ ሆኖም የተጫዋቹ ወኪል ‹‹ሲሴ ቁማርተኛ አይደለም›› ሲል ማስተባበያ ሰጥቶለታል፡፡ የካዚኖው ኩባንያ ቃል አቀባይ ግን ሲሴ ከአንድ ጊዜ በላይ ወደ ቁማር ቤት ለመምጣቱ ማረጋገጫ ሰጥቷል፡፡ በቁማር ቤት መገኘቱን እንጂ ቁማር መጫወቱን ግን አልገለፀም፡፡
የኒውካስል ከተማ ከንቲባ ዲፑ አሃድ ሲሴ ማሊያውን አልለብስም ባለበት ሰዓት ላይ ለተጨዋቹ ድጋፋቸውን ሰጥተው ነበር፡፡ በኋላ አቋሙን መቀየሩ ግን ሰውየውን ለትችት የዳረጋቸው ይመስላል፡፡ በተለይ በቁማሩ ቤት የመገኘቱ ዜና ከንቲባውን አበሳጭቷቸዋል፡፡ አሃድ ለቢቢሲ በሰጡት መግለጫ እንዲህ ብለዋል፡፡ ‹‹በድርጊቱ በጣም አፍሬያለሁ፡፡ እኔ ብቻ ሳልሆን በአቋሙ የደገፉትን ሁሉ አሳፍሯል፡፡ በቁማር ቤት መገኘቱ (ቁማር ባይጫወትም እንኳን) መጥፎ መልዕክት ያስተላለፈ ይመስለኛል››
ለሃይማቱ ተከታዮች ፆም ሌላው ግዴታ ነው፡፡ ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያ ድረስ ከምግብ፣ መጠጥ፣ ማጤስ እና ወሲብ መፈፀም መራቅ ግድ ነው፡፡ በረመዳን ወር ሙስሊሞች በዚህ ይተጋሉ፡፡ ወቅቱ የፀሎት ጊዜም ነው፡፡ በዚህ ወር ሙስሊሞች ከበዛ መዝናናት ሳይቀር ይታቀባሉ፡፡
ለስፖርተኞች ደግሞ ፈታኝ ጊዜ ነው፡፡ አንዳንዶች ጭራሹኑ አይጾሙም፡፡ ሌሎቹ ደግሞ የመጣውን ሁሉ ተጋፍጠው ይፆማሉ፡፡
ከማይፆሙት መካከል አንዱ ኒኮላ አኔልካ ነው፡፡ በፆም ወቅት ጉዳት እንደሚደራረብብኝ አረጋግጫለሁ ያለው ፈረንሳዊ የማይፆምበትን ምክንያት አቅርቧል፡፡ አንዳንድ አሰልጣኞች ደግሞ ተጨዋቾቻቸው እንዳይፆሙ ይከለክሏቸዋል፡፡ እንደማሩዋን ሻማክ ያሉት ደግሞ የአሰልጣኞችን ትዕዛዝ ወደ ጎን በማለት የሃይማኖታቸውን ግዴታ ይወጣሉ፡፡ በአንድ ወቅት ካኑቴ ሲናገር ‹‹በፆሙ ወቅት የማደርገውን ሁሉ የቡድን ጓደኞቼ በአንክሮ ይከታተላሉ›› ብሏል፡፡ ይከታተሉ እንጂ በፀሎቱ ጊዜ አይረብሹትም፡፡ እምነቱን ያከብሩለታል፡፡ ‹‹ስለዚህ እየጾምኩኝ መጫወቴ የተለመደ ነው›› ይላል፡፡
ሙስሊም ተጨዋቾች በረመዳን ወር በተቻላቸው መጠን ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ቢገደቡላቸው አይጠሉም፡፡ ፆሙን በአግባቡ ለመፆም ሲሉ ነው፡፡ በአብዛኛው በሙስሊሞች የተገነባ ቡድን ያለው የግብፁ አል አህሊ ክለብ ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡ የካይሮው ክለብ በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ከኦርላንዶ ፓይሬትስ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ከሐምሌ 28 ወደ ነሐሴ 3 ቀን 2005 እንዲቀየርለት ጠይቆ የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን ጥያቄውን ተቀብሎ ቢሆን ኖሮ ጨዋታውን ከፆሙ መጠናቀቅ በኋላ ይደረግ ነበር፡፡ ሆኖም ካፍ ጨዋታው በተያዘለት መርሐ ግብር እንዲቀትል (እንዳይቀየር) ወስኗል፡፡
አፍሪካዊያን እግርኳስ ተጨዋቾች ሁሉ ሙስሊሞች አይደሉም፡፡ ወይም ሙስሊም ተጨዋቾች ሁሉ አፍሪካዊያን ናቸው ማለት አይደለም፡፡ ግን የአፍሪካዊያን ሙስሊም እግርኳስ ተጨዋቾች ቁጥር ብዙ ነው፡፡
muslimpopulation.com እንደተሰኘው ድረገፅ መረጃ ከሆነ ከግማሽ በላይ አፍሪካዊያን የእስልምና እምነት ይከተላሉ፡፡ ለእንግሊዝ አገር ሙስሊም ተጨዋቾች ሃይማኖታዊ ግዴታቸውን በመወጣት እንዲጫወቱ ለማድረግ ድጋፍ ሰጪ ተቋም አላቸው፡፡ ቀድሞ ያልነበረውን ይህን አገልግሎት የሚሰጠው ተቋም በ2011 ናታን ኤሊንግተን በተባለ የክሪው አሌክሳንድራ አጥቂ የተመሰረተው የሙስሊም ተቋም በ2011 ናታን ኤሊንግተን በተባለ የክሪው አሌክሳንድራ አጥቂ የተመሰረተው የሙስሊም እግርኳስ ተጨዋቾች ማህበር ነው፡፡ በሊቨርፑሉ የስፖርት ህክምና ቡድን ኃላፊ ተጨዋቾች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ምክር ይሰጣል፡፡ በማፍጠሪያ ሰዓት ጥቂት ብቻ እንዲመገቡና በኋላም በዛ ያለውን ምግብ እንዲያስከትሉ የዶክተሩ መመሪያ ይመክራል፡፡ በተጨማሪም ማህበሩ ከቢቢሲ ጋር በመተባበር ‹‹THE MUSLIM PREMIER LEAGUE›› የተሰኘ ጥናታዊ ፊልም ለማዘጋጀት እየሰራ ይገኛል፡፡ ፊልሙ በእንግሊዝ ከፍተኛው የእግርኳስ ዲቪዚዮን ውስጥ ሙስሊም ተጨዋቾች የሚገጥማቸውን ጉዳዮች ይዳስሳል፡፡ በ20 ዓመቱ የሊግ ታሪክ ሊጉ በሙስሊም ተጨዋቾች ላይ ያሳደረውን አዎንታዊና አሉታዊ ተፅዕኖ ሁሉ በፊልሙ ላይ ይዳስሳል፡፡
Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=6641
“አገራችንን በእርቅ እንታደጋት” ዶ/ር ተጋ
August 24, 2013 03:00
የኢህአዴግ ባለስልጣኖችና ደጋፊዎች ከየትኛውም ዜጋ በላይ ዋስትና እንደሚፈልጉ በመግለጽ ዶ/ር ተጋ ለንዳዶ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ተናገሩ። በአገራቸው ጉዳይ ላይ በተለይም በዕርቅ ዙሪያ በርካታ ጽሁፎችን ሲያቀርቡና ሲንቀሳቀሱ የቆዩት ዶ/ር ተጋ ለንዳዶ በኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ በኃላፊነት ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን ከአገራቸው ውጪም በኬንያ፣ በሞዛምቢክ፣ በስዊትዘርላንድና በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች በከፍተና ኃላፊነት ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ በተለይም በዎርልድ ቪዥን፣ በተባበሩት መንግሥታ፣ በዓለምአቀፍ አብያተክርስቲያናት ካውንስል፣ … የሰጡት የዓመታት አገልግሎት ተጠቃሽ ነው፡፡ በአገር ውስጥና በውጪ አገራት የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ ትምህርታቸውን የተከታተሉት ዶ/ር ተጋ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የዕርቅ፣ የሰላምና የፍትሕ ሒደት ውስጥ የተጫወቱት መጠነኛ ሚና በአገራቸው ተግባራዊ ሆኖ ለማየት የሚመኙና ለዚያም የሚቻላቸውን ጥረት ሁሉ ሲያደርጉ መቆየታቸው እስካሁን የሠሩት ሥራ ምስክር ነው፡፡ ከዚህም ሌላ ዶ/ር ተጋ ለንዳዶ የአገር ውስጥና የውጭ ስድስት ቋንቋዎችን አቀላጥፈው የሚናገሩ ናቸው፡፡
“እውነተኛ እርቅ የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ ነን” የሚሉት ዶ/ር ተጋ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በመረዳት አገራችን ከምትገኝበት አደጋ መታደግ የሁሉም ዜጋ ግዴታ እንደሆነ አመልክተዋል። በማያያዝም በደል ሲበዛ ህዝብ እንደሚያምጽ በመጠቀስ ሳይረፍድ ሁሉም ወገኖች ለእርቅ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጠይቀዋል።
እርቅና ሰላም ለማውረድ የሚችሉ ዜጎች አድፍጠው መቀመጣቸውን የጠቆሙት ዶ/ር ተጋ “የፖለቲካ መናኞች” ያሉዋቸውን እነዚህ ዜጎች ከተደበቁበት በመውጣት ባገራቸው ጉዳይ ተሳታፊ ሊሆኑ እንደሚገባ አሳስበዋል።
እውነተኛ እርቅ ቢጀመርና፣ ለማስታረቅ የሚመጥን ስብእና ያላቸው ወገኖች የሚካተቱበት አስታራቂ ቢሰየም ህዝብ እውቅና ለመስጠት እንደማይቸገር ያስታወቁት ዶ/ር ተጋ “ከኢህአዴግ ወገን እርቅ የሚፈልጉና ለልቡናቸው የቀረቡ ሰዎች አሉ። እነሱም ሰው ናቸውና ሰላም ይፈለልጋሉ። ራሳችሁን መናኝ ያደረጋችሁ ከተደበቃችሁበት ውጡና ኢትዮጵያን እናድን” ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል። ሙሉ ቃለ ምልልሳቸው እንደሚከተለው ተቀናብሯል።
ጎልጉል፦ በተደጋጋሚ ስለ እርቅ ይናገራሉ። በርግጥ መፍትሔ ይኖረዋል?ዶ/ር ተጋ፦ ከእርቅ ውጪ ምንም አማራጭ የለም። አለ?
ጎልጉል፦ አሁን ኢህአዴግ ከያዘው አቋም አንጻር “እርቅ ዋጋ የለውም” የሚሉ አሉ፤ዶ/ር ተጋ፦ ስለነዚህ ወገኖች በተለይ የምለው ነገር የለም። በኔ እምነት እርቅ፣ ትክክለኛው የእርቅ መንገድ ተሞክሯል የሚል እምነት የለኝም። ስለዚህ ትክክለኛው እርቅ፣ እውነተኛው አርቅ መሞከር አለበት። እኔ እንደምረዳው ከሁሉም ወገን ትክክለኛ እርቅ ከቀረበ ተቀባይ የማይሆንበት ምክንያት የለም።
ጎልጉል፦ትክክለኛ እርቅ ሲሉ ምን ማለትዎ ነው?ዶ/ር ተጋ፦ ከፍቅርና የሚመነጭ ፍርሃት ሰዎች አምነው እንዲገዙ ያደርጋቸዋል። ፍርሃት ስል አምነው ለሰየሙት መንግሥት ክብር መስጠትና መገዛትን ነው። በሌላ በኩል ደግሞ መሳሪያ ያላቸውና ህግ ያረቀቁ ክፍሎችም ህዝብን መግዛት ይችላሉ። እነዚህ ክፍሎች እኔን ምሰል። እኔ የምልህን አድርግ። አንተ ቦታ የለህም። የአንተ ድርሻ መገዛትና መገበር ብቻ ነው። አንተ ዝም ብለህ ከመገዛት ውጪ ሌላ ተግባርና ድርሻ የለህም በማለት በጉልበት ይገዛሉ። ልክ አሁን እንደሚደረገው ማለት ነው። በሌላ ወገን “አማራጭ ነን” ብለው በጉልበት እየገዛ ያለውን ለመገልበጥ የሚታገሉ አሉ። ገለልተኛ ሆነው የሚኖሩና የሸሹ ወገኖች አሉ። እነዚህ የሸሹ ሰዎች “የፖለቲካ መናኞች” ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ ሌሎችንም አካትቶ ለመታረቅ ሲስማሙ ትክክለኛው እርቅ ይመጣል። ሳይሞከር አይሳካም ማለት አይቻልምና እንሞክረው።
ጎልጉል፦ ያልተቻለው እኮ እነዚህን ወገኖች ማሰባሰብ ነው? በተለይም ኢህአዴግን ወደ እርቅ የሚገፋው ጉዳይ የለም የሚሉም ወገኖች አሉ። ኢህአዴግ ምን አስፈርቶት ወደ እርቅ ይመጣል? የሚሉ አሉ፤ዶ/ር ተጋ፦ ለጊዜው ሃይል አለኝ ብሎ ከተራራ ላይ አልወርድም። መሳሪያ አለኝና እርቅ አይበጀኝም። ጡንቻ አለኝና ሰላም አያሻኝም በማለት ኢህአዴግ የሚያከር ከሆነ የተጎዱ፣ የተረገጡ፣ የተገፉ፣ የከፋቸው፣ የባሰባቸው ቀኑ ሲደርስ “አታስፈልግም” ብለው ይነሳሉ። ዓለም ብዙ አሳይታናለች። የህዝብ ቁጣ ሲነሳ የሚደርሰው አደጋ የከፋ ነው። እኔን ዘወትር የሚያስጨንቀኝ ይህ ነው። የኢህአዴግ ሰዎችም ቢሆኑ ሰዎች ናቸውና ከደጋፊዎቻቸው ጭምር ይህንን ሳያስቡት ውለው ያድራሉ ብዬ አላስብም። ደግሞም ያስባሉ። እንደውም ከማንኛቸውም በላይ የኢህአዴግ ደጋፊዎች እውነተኛ እርቅ የሚመኙበት ወቅት ላይ ለመሆናቸው ጥርጥር የለውም። ዋናው ጉዳይ ግን እንዴት …
ጎልጉል፦ ኢህአዴግ እርቅ ይፈልጋል እያሉ ነው?ዶ/ር ተጋ፦ በሚገባ። የኢህአዴግ አመራሮችና ደጋፊዎች እኮ ሰዎች ናቸው። አሁን አገሪቱ ላይ ያለው አደጋ ያሰጋቸዋል። ከሁሉም በላይ ሰላም ለነሱም ያስፈልጋቸዋል። ያለ ስጋት ተራ ሰው ሆነው መኖር የሚፈልጉ አሉ። የግፍና የጭቆና መጠን ሲያልፍ ህዝብ እንደሚነሳ ጠንቅቀው ያውቃሉ። የግፈኛ መሪዎች መጨረሻ ምን እንደሚመስል ይረዳሉ። ችግሩ ያለው እነሱና ደጋፊዎቻቸው ወደ እርቅ እንዲመጡ የሚኬድበት መስመር አግባብ ያለው መሆኑ ላይ ነው። የመተማመን ችግር አለ።
ጎልጉል፦ እርቅ የጀመሩና አሁንም እየሰሩ ያሉ አሉ?ዶ/ር ተጋ፦ ካሉ ጥሩ ነው። እኔ ግን የማወራው ሌሎች ስለጀመሩት እርቅ አይደለም። እኔ የምናገረው የእውነተኛው እርቅ መንገድ ለገባቸው፣ የእርቅ ሃሳብ ላላቸው፣ ያልተነካኩና ለእርቅ ተግባር ቢነሱ የህዝብ ይሁንታና አመኔታ ማግኘት ለሚችሉ፣ ኢህአዴግም አክብሮ ሊያነጋግራቸው ፈቃደኛ ይሆናል ብዬ ለማምንባቸው ክፍሎች ነው። እርቅ ጀመሩ የሚባሉትን እነዚህን ሰዎችም ሆኑ ክፍሎች አላውቃቸውም። የምናገረው ቢጀምሩት ይሳካላቸዋል ብዬ ለማምንባቸው ሰዎች ለህሊናቸው ነው። የአገራችን ጉዳይ ያገባናል ለሚሉ ጨዋ ስብዕና ላላቸው ወገኖች ነው። እንግዲህ ይህንን ስል ከሁሉም ወገን ኢህአዴግን ጨምሮ ነው። አሁን አገራችን ያለችበት አሳሳቢ ወቅት ጤና ለነሳቸው፣ የወደፊቱ ትውልድ እድልና እጣ ፈንታ ግራ ላጋባቸው የኢትዮጵያ ልጆች ነው።
ጎልጉል፦ እውነተኛ እርቅ ምንድ ነው?ዶ/ር ተጋ፦ ስለ አቀራረቡ መናገሩ የሚሻል ይመስለኛል። ከላይ የጠቀስኳቸው ክፍሎች ውስጥ አገራችንን ሊታደጉ የሚችሉ፣ የመጪውን ትውልድ መከራ ሊገፉ የሚችሉ ነገር ግን ዝምታን የመረጡ የተከበረ ስብእና ያላቸው ወገኖች አሉ። እነዚህ ዝምታን የመረጡ ወገኖች ዝምታን የመረጡበት በርካታ ምክንያቶች ይኖራቸዋል። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከውስጥም ሆነ ከውጪ ስድድብ ነው። አንዳንዴ ቃላት እንኳ አይመረጥም። ሰው በስድብ ፖለቲካና ባለመከባበር የሚደረገው አተካሮ የሰለቸው ይመስለኛል። አንግዲህ እንዲህ ያለው መንገድ አልመች ብሏቸው ዝም ያሉትን ከተሸሸጉበት እንዲነሳሱ ማድረግ የመጀመሪያው ስራ ነው። ሌላው እርቅ የምትጠይቀውን ክፍል ማክበር ነው። እየዘለፍክና እያዋረድክ እርቅ መጠየቅ በባህላችንም ቢሆን አያስኬድም። በመከባበር ልዩነትን ማሳየትና ተቃውሞን መግለጽ የሚቻልበት መንገድ ሲፈጠር አድማጭ ማግኘት ይቻላል። በዚህ መልኩ መነጋገር ይጀመራል። እውነተኛ እርቅ የሚጀመረው የእርቁ አጀማመር ክብር የተሞላበት ሲሆን ነው። ሲጀመር መከባበርና የህዝብን ይሁንታ ማግኘት ከተቻለ የቀረው ጉዳይ ሂደት ነው የሚሆነው። ራሳቸውን ያከበሩና የጸዳ ማንነት ያላቸው ወገኖች ከየትኛውም ወገን ድጋፍ አላቸው። ከበሬታም አይነፈጉም። ኢህአዴግ ራሱም ቢሆን ሊገፋቸው አይችልም። አላማቸውና መሰረታቸው እርቅ ማውረድ መሆኑ ከተረጋገጠ ሊገፉ ወይም እምቢ ሊባሉ የሚችሉበት መንገድ የለም። ሁሉም ነገር የሚመነጨው ከስብዕናቸው ነውና ስብዕናቸው ያማረ ሰዎች ተሰባስበው እርቅ ላይ ቢሰሩ የሁሉም ስጋት ተቀረፈ ማለት ነው። ሌላ ትርጉም ካልተሰተው በቀር እርቅ አሁን ላለችው ኢትዮጵያ ፈውሷ ነው።
ጎልጉል፦ የሐይማኖት መሪዎች ሚና ምን ሊሆን ይችላል?ዶ/ር ተጋ፦ የሐይማኖት መሪዎች ነው ያልከው? እንደው ለመሆኑ እዛ ደረጃ የደረሱ አሉ? ካሉ ጥሩ ነው። እኔ ግን እስካሁን አላየሁም። የራሳቸው የግል አመለካከት ቢኖራቸውም ለጊዜው እሱን ወደ ጎን አድርገው ለእርቅ ቢሰሩ ደግ ነው። ግን …
ጎልጉል፦ ቄስ ገመቺስና ቄስ ኢተፋ ጎበና የጀመሩት እርቅ ነበር፤ዶ/ር ተጋ፦ ለትግል መንስዔ የሆኑ ሰዎች የእርቅ አፋላላጊ መሆን የሚችሉ አይመስለኝም። ከጅምሩ የህዝብን ይሁንታ ማግኘትና አለመነካካት ያልኩት እዚህ ጋር ይመጣል። ከቤተክርስቲያን ሃላፊነት በላይ በእርቅና በሰላም ፍልስፍና ማመን ይቀድማል። ራሳቸውን ለሰላምና ለእርቅ ፍልስፍና ያስገዙ ሰዎች የእርቅን ሂደትና የሚያስከፍለውን ዋጋ ስለሚረዱ እንዲህ አይነት ሰዎች ቢሆኑ ይመረጣሉ ባይ ነኝ። አሁን የጠቀስካቸው ወገኖች የጀመሩት ስራ ድጋፍ የሚያሻው ደረጃ ከደረሰም ማገዝ ነው።
ጎልጉል፦ በአንድነት ያምናሉ?ዶ/ር ተጋ፦ አንድነት የተሰጠን ነው። እምነት ነው። በፍጹም ሊፋቅ አይችልም። አንድነት ውስጥ ልዩነት፣ በልዩነት ውስጥ ደግሞ አንድነት አለ። የምናምረው በልዩነታችን ነው። በልዩነታችን ውስጥ የሚፈጠረው አንድነት ደግሞ ያደምቀናል። ልዩነት በየጊዜው የሚያድግ፣ ወደፊትና ወደኋላ የሚለጠጥ የላስቲክ ይዘት ያለው ነው። ስለዚህ ይህንን እንደ ላስቲክ የሚለጠጥ ልዩነት ስንይዘው፣ “ያንተ ማንነት እኔን አይረብሸኝም” የሚለው እሳቤ ውስጥ ሁልጊዜም መኖር እንችላለን። ያንተ ቋንቋ፣ ማንነት፣ አስተሳሰብ፣ አያስፈልገኝም የሚል ጉዳይ ከተነሳ የላስቲክ ይዘት ያለውን ልዩነት ባህሪውን ወደሚሰበርና የሚቀነጠስ ቁስ ይቀይረዋል። እንዲህ ያለው እርምጃ አደጋ አለው። እኔ እንግዲህ እንዲህ ያለውን አስተሳሰብ ከሚቃወሙ የአንድነት አማኞች ውስጥ ነኝ …
ጎልጉል፦ ስለ እርቅ እንመለስና የውጪ ሃይሎች /መንግስታት/ ካልገቡበት አይሆንም የሚሉ አሉ፤ በተለይም ተጽዕኖ ፈጣሪ አገሮች፤ዶ/ር ተጋ፦ እስከማውቀው ሕዝብ እውቅና የሰጠው እርቅ ስለመከናወኑ አልተሰማም። እኔ በግል ህዝብ እውቅና የሰጠው እርቅ ስለመኖሩ መረጃ የለኝም። በመጀመሪያ እርቅ በጓዳ ሲሆን ክብር የለውም። እርቅ በግልጽና ባደባባይ መሆን አለበት። ከላይ የገለጽኳቸው ወገኖች ከተሸፈኑበት መጋረጃ ከወጡና ለእርቅ ከሰሩ ብዙ ርምጃ መራመድ ይቻላል። የውጪ ሃይሎችን ማካተት ተገቢ የሚሆንበት አግባብ ብዙ ነው። እንደውም በገሃድ እርቁ ሲጀመር ለእርቁ ስራ የሚተባበሩ አገራትም አብረው መገለጽ አለባቸው። ለምሳሌ በኤርትራ ጉዳይ ላይ ኖርዌይ ብዙ ሚና ተጫውታለች። በወቅቱ ሚናዋ ደስተኛ ባልሆንም አስፈላጊ የሆኑ አገሮች እንዲካተቱ ማድረግ ተገቢ ይመስለኛል።
ጎልጉል፦ በተደጋጋሚ ዝምታን የመረጡ እንዲነሱ ይጠይቃሉ። በውል ስም ጠርተው ለዚህ ተግባር ተነሱ የሚሏቸው ወገኖች ካሉ?ዶ/ር ተጋ፦ ብዙ ታሪክ መለወጥ የሚችሉ ወገኖች አሉ። ራሳቸውን ከአገራቸው ፖለቲካ አግልለው የመነኑ አሉ። ራሳቸውን የፖለቲካ ባህታዊ ያደረጉ አሉ። እነዚህ ባህታዊ ፖለቲከኞች እንዴት እንዲቀሳቀሱ ማድረግ እንደሚቻል ያሳስበኛል። ብዙ እርቅ ላይ መስራት የሚችሉ ወገኖች አሉ። እነዚህም ወገኖች ከሸፈቱበት የ”አያገባኝም” መንገድ ተመልሰው ማየት እፈልጋለሁ። ስለዚህ ድንገት ቢሰሙኝ ብዬ ነው ደጋግሜ የጠቀስኳቸው።
ጎልጉል፦ ፖለቲከኛ ነበሩ? አሁንስ?ዶ/ር ተጋ፦ ፖለቲከኛ አይደለሁም። አጥብቄ የምጠየፈው ነገር ነው። አንዴ እዚህ፣ አንዴ እዚያ የመርገጥ ባህሪ የለኝም። የመገለባበጥ ነገር አይገባኝም። አቋራጭ ብሎ ነገር አላውቅም።
ጎልጉል፦ ግን በቂ ልምድ ያለዎት ይመስላል፤ዶ/ር ተጋ፦ (ሳቅ ብለው) … ልምድ!! ስለ አገራችን ፖለቲካ አንድ ነገር ልበል። የእኛ ህዝብ ቦይ ነው። መንገድ ካሳየኸው ዝም ብሎ ይጎርፋል። አሁን ታዲያ ቦዩ በዛ። ቦዮቹ ደግሞ ትንንሽ ሆኑ። ትንንሽ ስም ያላቸው ሆኑና እንደ ስማቸው ትንሽ፣ ትንሽ ሰዎችን ይዘው ቀሩ። እነዚህ ትንንሽ ቦዮች የጥቂት ብልጣብልጦች መጠቀሚያ ሆኑ። ባህሪያቸውና ተፈጥሯቸው ትንሽ በመሆኑ ጥቂቶች አትራፊ ሆኑና አብዛኞች ከሰሩ። ይህ አካሄድ ያላስደሰታቸው አብዛኞች ራሳቸውን አቀቡ። አድፋጮች በዙና /silent majority/ ተባሉ። ከስማቸው እንደምንረዳው እነሱ ይበዛሉ። አሁን ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት እነዚህ ዝምተኛ፣ ባህታዊ ፖለቲከኞች፣ የመነኑ ዜጎች ተመልሰው ለእርቅና ለሰላም እንዲሰሩ ማሳሰብ የሁሉም ቀና ዜጋ ተግባር ሊሆን ይገባል። እኔ እንግዲህ እንደዚህ አስባለሁ። የተደበቁ ተመራማሪዎች አሉ። ሌሎች አገራትን የሚጠቅሙ ክቡር ዜጎች አሉን። አገራቸውን የሚወዱ ህዝብን የሚፈሩ አሉ። ከሁሉም በላይ ለህሊናቸው የሚኖሩ ዜጎች አሉ። ኢትዮጵያ የልጆች ደሃ አይደለችም። እነዚህ ዜጎች ለህዝብ ሲሉ፣ አገራቸው ሰላምና እርቅ እንዲወርድላት ሲሉ ከተደበቁበት ሊወጡ ይገባል።
ጎልጉል፦ ከህወሃት ሰዎች ጋር ይተዋወቃሉ?ዶ/ር ተጋ፦ የቀድሞውን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ስዩም መስፍንን አውቃቸዋለሁ፤ አብረን ተምረናል። ባለስልጣን ከሆኑ በኋላ ተገናኝተንም ነበር። በግል በእርቅ ዙሪያ ላነጋግራቸው እችላለሁ። ሌሎችም ሰዎች አሉ። ኢህአዴግ ውስጥ ቀና ሰዎች እንዳሉ መታመን አለበት። ቀና የትግራይ ልጆች አሉ። የወደፊቱ ችግር የሚያሳስባቸው ጥቂት አይደሉም። ደጋግሜ እንደነገርኩህ ዋስትና የሚናፍቁ ባለስልጣኖች ብዙ ናቸው። ሰላም የሚመኙ ብዙ ናቸው። መንገዳቸውን መመርመር የሚፈልጉ ጥቂት አይደሉም። ግን በስድብና በጥላቻ ሊሆን አይችልም። በመከባበር የሚመሰረት መቀራረብ ወደ አንድ የእርቅ ሃሳብ ያመጣል። ጊዜ ቢወስድም መጀመር አለበት። ሲጀመር ግን በክብር መሆን አለበት። ህዝብም እውቅና የሚሰጠው ሊሆን ይገባል።
ጎልጉል፦ እርስዎ የሚያምኑበት እርቅ በዋናነት ምን መያዝ አለበት?ዶ/ር ተጋ፦ እርቅና ሰላም ከፍትህ ጋር። ፍትህ የሌለበት እርቅ ዋጋ የለውም። ሰላምም አያመጣም። ግብጽ ጥሩ ምሳሌ ናት። አሁን የተነሳውን የፕሬዚዳንት ሙርሲን ደጋፊ ምን ታደርገዋለህ። ፍትህ ካላገኘ ለመሞት ተነስቷል። በሌላ በኩል ሙርሲን አውርደው የተቀመጡ አሉ። ለሙርሲ ደጋፊዎች ምላሽ ቢሰጥ አውርደው የተቀመጡትና የፈለጉትን ለመምረጥ ጊዜ ገደብ የተቀመጠላቸው ይነሳሉ። ሲጀመር ፍትህና እርቅ ተጣምረው ባለመከናወናቸው ችግሩ እየተባበሰ ሄደ። ስውር ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው ማለቴ ነው። ስለዚህ እርቅና ፍትህ የሚለያዩ ነገሮች አይደሉም። ፍትህ ያለበት እርቅ እንዲሰፍን ተግተን መስራት አለብን። አገራችን ያለችበት ሁኔታ ቸል የሚባልበት አይደለም። በኋላ ሁላችንንም ይቆጨናል። እርቅ ላይ ትኩረት ማድረግ ግድ ነው። የፖለቲካ ለውጥ እንኳን ቢኖር የተዘራውን ክፉ ዘር ለማክሰም እርቅ ግድ ነው።
Friday, August 23, 2013
የወጣቱ የመጥለፍ ፖለቲካ በ” ይልቃል አዲሱ ልደቱ…? ” ፀሁፉ ውስጥ
በጥያቄ ምልክትና እና በቃለ አጋኖ የታጀበውን ‘’ይልቃል አዲሱ ልደቱ” በሚል ርዕስ ወጣት ዳዊት ስለሞን በብዕር ስም /አይናለም/ የተፃፈውን ባለ ብዙ ሀሳብ ፅሁፍ አነበብኩት ፡፡ አንድ ፅሁፍ ሲፃፍ አንባቢ ሊታዘብ ይችላል ሰለዚህ እውነት ላይ እና እየታዩ ካሉ ነባራዊ ሁኔታዎች አንፃር መቃኘት አለበት የሚለው ዋና ጉዳይ በዚህ ፀሁፍ ውስጥ ለኔ አልታየኝም ፡፡ በፅሁፉ ውስጥ አንባቢን ለማሳመን የተደረጉ ውጣ ውረዶች ከመጥቀሴ በፊት ፀሀፊው አባል በሆነበት አንድነት ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ ውስጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተመለከትኩትን የሚበረታታ ጉዳይ ከማሳሰቢያው እጠቅሳለሁ፡፡
ማሳሰቢያ ‘’ይልቃል አዲሱ ልደቱ” ፅሁፍ ፀሀፊ ዳዊት ሰለሞን የአንድነት ፓርቲ ልሳን የሆነው ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ኣዘጋጅ ለመሆኑ አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የአንድነት አባል ስለነገረኝ ከዚህ በታች የምጠቀመው የብእር ስሙን ሳይሆን ዳዊት የሚለውን ዋና ስሙን መሆኑን አሳውቃለሁ፡፡
መኢአድ ሲባል ኢ/ር ሀይሉ ሻወል፣ ደቡብ ህብረት ሲባል ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ፣ ኦብኮ ሲጠቀስ ዶ/ር መረራ ጉዲና… የፖለቲካ ተክለ ሰውነት ለብሰው ብቅ ይሉብናል፡፡ ይህ የፖለቲካ ተክለ ሰውነት በአንድት ውስጥም ግዝፈቱን ሳይቀንስ ተንሰራፍቶበት ቆይቷል፡፡ ይህ ማለትም አንድነት ሲባል በየደቂቃው የሚለዋወጥ አቋም ያለው ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው እና ባለመልካም ባህሪው ዶ/ር ሀይሉ አርአያ ድቅን ይሉብን ነበር እነአቶ አስራት ጣሴን አስከትለው፡፡ ወጣት ዳዊትም በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ የሚታዩ ችግሮች ብለው ከጠቀሱዋቸው መካከል የግለሰብ ተክለ ሰውነት መገንባት አንዱ ነው፡፡
እኔም የግለሰብን ተክለ ሰውነት አንዱ መስፈርት አድርጌ ፓርቲዎችን ስገመግም አንድነት አሁን ካሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ውስጥ የተሻለ ነው እንድል ያደረገኝ ከግለሰብ ትከሻ ላይ ወርዶ አበረታች የሚባል የቡድን ስራ ማክናውን ላይ በመሆኑ ነው፡፡
የተመለከትኩትን ጠንካራ ጎን ከገለፅኩ በኋላ የፓርቲው አባል የሆኑት ወጣት ዳዊት ፅሁፍ ላይ ላተኩር፡፡ ሀሳብን በነፃነት ለመግለፅ ያደረገውን ጥረት በማድነቅ ፅሁፉ መጀመሪያ ላይ የጠቀሱት የደርግ/ የኢህአፓ /የመኢሶን ፖለቲካዊ መጠላለፍ ዛሬ ላይ እንዲመጣ ወይም ዛሬ ላይ ያለው የመፈራረጅ ፖለቲካ እንዲቀጥል ታጥቀው የተነሱ ነው የሚመስለው፡፡ እንዴት! ማለት ጥሩ….. በአዲስ መስመር ከመቀጠሌ በፊት እኔ የሰማያዊ ፖርቲ አባልም ደጋፊም አለመሆኔ ሊታወቅ ይገባል፡፡
አንባቢን ለማሳመን እና ሰማያዊ ፓርቲ የወጣቶች ስብስብ መሆኑን ለማጣጣል የአቶ ልደቱ ወጣት መሆን በመጥቀሥ በጥሩ ሁኔታ እየተቀሰቀሰ ያለውን ፖለቲካ ለመጥለፍ ‹‹አዲሶቹ ጎጆ ወጪዎች ከመጀመሪያው ቤታቸው ሲወጡ በአብዛኛው ባዶ እጃቸውን አይሆኑም፣የእናት ፓርቲያቸውን የፖለቲካ ፕሮግራም፣አደረጃጀትና አባል ይዘው ሹልክ ይላሉ፡፡ለዚህ እንደምሳሌ ኢዴፓና ሰማያዊ ፓርቲን መውሰድ ይቻላል፡፡›› ይሞክራሉ፡፡ እኔም አንድ የመጥለፉ መንገድ ልከተልና ፀሀፊውን ልጠይቀው፡፡ ቅንጅት የአራት ፓርቲዎች ጥምረት ነው፡፡ መሪዎቹ ታስረው ሲፈቱ በጋራ መቆም አቃታቸውና የየራሳቸውን ደጋፊና አባል በመያዝ ለአራት ተሰነጣጠቁ፡፡ከግንቦት 7 በስተቀር ሁሉም የሰላማዊ ትግል መርጦ የቅንጅቱን መንፈስና ፕሮግራም ለማስቀጠል በያለበት ይንቀሳቀሳል፡፡ ከነዚህ ውስጥም አንድነት አንዱ በመሆኑ የእናት ድርጀቱን አባል ፕሮግራም ይዞ ሹልክ አለ ማለት ነው ወይስ አንድነት የተለየ ፕሮግራም አረቀቀ? ይህን ለመመለስ የቅንጅትንም የአንድነት በደንብ ፕሮግራሞች ማየት ያስፈልጋል እንዳትረሳው!
የሰማዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር ላይ ያስቀመጠው ቅሬታ / ግን ሰይጣናዊ ቅናት ብለው በትክክል ይገልፀዋል/ ጠቅለል አርጌ ለመግለፀ በሁለት መክፈል እፈልጋለሁ፡፡ ሊቀመንበሩ ላይ የቀረበው ቅሬታ ለፖለቲካው በማሰብ በሚል እና ፀሀፊው ጎልቶ ለመውጣት ባለው ጉጉት የሚከተላቸው መንገዶች በሚሉ ፡፡
ለፖለቲካው በማሰብ
ኢ/ር ይልቃል /የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር/ “ፓርቲዎች አሉ ብለን አናምንም ተባበሩ የምትለን ከማን ጋር ነው ? መድረክ ምን ሰራ አንድነትና መድረክ እየተባሉ አይደለም? አንድነት ውስጥ የገባው ብርሃን ወጥቷል እኛ ከማን ጋር እንተባበር ? ብለዋል ብሎ ወጣት ዳዊት ይኮንናል፡፡ የኢ/ር ይልቃል ንግግር ላይ ያለውን ስህተት ለማሳየት ፓርቲዎቹ የሰሩትን ምንም መረጃ ማቅረብ ስላልቻለ በደፈናው በህብረት ለመስራት አንፈልግም ብለዋል ሲል ተንከባሎ ያልፋል፡፡ የመድረክ አባል ፓርቲዎች የደቡብ ህብረት ከፕ/ር በየነ ሳምሶናት ውስጥ መውጣት ሳይችል፣ ኦፍዴን ከአቶ ቡልቻ የግል ንብረትነት ሳያልፍ፣ ኦብኮ ከዶ/ር መራራ የኮሜዲ ምሽት ሳይላቀቅ ፣አረና አባላቱ በነፃ ዝውውር ለሰማያዊ ፓርቲ እየፈረሙ ባሉበት ሰአት እና አንድነት በኣዛውንቶችና በወጣቶች መሀክል በሚደረግ ገመድ ጉተታ ፖለቲካ ውስጥ ነው ያለው ስለዚህ ከማን ጋር በህብረት ይስራ ነው የሚባለው፡፡ በተጨማሪም ብርሀንም ከአንድነት የወጣው ገመድ የጉተታ ውጤት ይዞት የሚመጣው ጦስ አስግቶት ነው፡፡ ታዛቢ ስላለ እውነቱ ይህ መሆኑን መግለፅ ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ የተቀረበው ቅሬታ ለፖለቲካው በማሰብ አደለም ለማለት እደፍራለሁ፡፡
በተጨማሪም አንድነትን ጨምሮ ሁሉም የመድረክ ፓርቲዎች ጥርት ያለ የፖለቲካ ፕሮግራም ስለሌላቸው መስማማት አልቻሉም ፡፡ ይህንን ስል በስሜት አለመሆኑን ለማስገንዘብ ሁለት ምሳሌ ልጥቀስ፡፡ የመሬት ጥያቄና የመገንጠል መብት ፓርቲዎቹ ከግንባርነት እንዳያልፉ ማነቆ ሆነው ስራ እዳይሰሩ ያደረጋቸውን ብቻ ማንሳት በቂ ነው፡፡ ይህም እውነት ሲገለጽ በሰማያዊ ፓርቲ ፕሮግራም ላይ የተቀረበው ቅሬታ ለፖለቲካው በማሰብ አይደለም ለማለት እገደዳለሁ፡፡
ጎልቶ ለመውጣት የሚደረግ ጥረት
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንድነት ከላይ እንደጠቀስኩት ከግለሰብ ስብእና ራሱን በማፅዳት የቡድን ስራን በመጀመር የሚያበረታታ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡ ይህም የቡድን እንቅስቃሴ ባለፉት ግዚያት እንደተመለከትነው በተለያዩ የክልል ከተሞች በመንቀሳቀስ የቀዘቀዘው የህዝብ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ዳግም እንዲያንሰራራ ሚዛን የሚደፋ አስተዋፆ አድረጓል፡፡ ለዚህም አበረታች ጅማሮ ከፊትም ከኋላም በመሆን ከፍተኛ አስተዎ ያደጉትን ግርማ ፣ዳንኤል እና በላይን የመሰሉ ወጣት ፖለቲከኞችን ማመስገን ያስፈልጋል፡፡ በዛውም ልክ ይልቃል ጎልቶ ለመውጣት ይፈልጋል ተብሎ እንደተከሰሰው በአንድነት ህዝባዊ ንቅናቄም ውስጥም በበርካታ ወጣቶች ላይ ጎልቶ የመታየት ፍላጎት ሲከሰት ከርሟል፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዱ ወጣት ዳዊት ይግኝበታል፡፡ እንዴት የሚል ጥያቄ ከተነሳም መልሱን ክዚህ በፊት ወጣቱ የሚያድጋቸውን ጎልቶ ለመውጣት የሚደረግ ድርጊቶች ላሳይ፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አንድነት ፓርቲ ውስጥ የተመለከታቸውን ህፀፆች እንደጋዜጠኝነቱ እንዲታረሙ በበሳል ብእሩ ሲጠቁም የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የጋዜጠኛውን ጥቆማ በመቀበል የታዩትን ችግሮች ለማረም ደፋ ቀና ብለዋል፡፡ ነገር ግን ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ የተባለው ብሂል በወጣቱ ዳዊት ላይ ተተግብሮ ‹‹ ተመስገን ደሳለኝ ሲያዳልጠው›› በሚል ጽኁፍ በአደባባይ ፓርቲውን ለምን ነካ ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት እፍኝ እውቅና ለማግኘት ሲታገል መድከሙ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ ይህ ተግባር በተመስገን ላይ ብቻ የተገደበ እይደለም ፡፡ ብዙ መጥቀስ ይቻላል ነገር ግን ዝም በመባሉ ያሸነፈ ስለመሰለው በተመሣሳይ ላሞኛችሁ አይናችሁን ጨፍሁ ብሎ በኢ/ር ይልቃል ላይ እንዲህ ሲዘምት ጎልቶ ለመውጣት በሚደረግ ጥረት የሚቀዘቅዘው የወጣቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ስላሳሰበኝ ነው ይህን ጽሁፍ ለመጻፍ የተገደድኩት፡፡
በአጠቃለይ የወጣቱ ፅሁፍ ለሀገራችን ፖለቲካ በማሰብ የቀረበ ሀሳብ ሳይሆን ጎልቶ ለመውጣት የሚደረግ ጥረት በመሆኑ የተጀመረው የህዝብን የማንቃት ስራ አዳክሞ ሀገሪቱን በአንባገነንነት ለሚመራው ኢህአዴግ ነው የሚጠቅመው፡፡ ስለዚህ ወጣት ዳዊት ገና ብቅ ብቅ የሚሉ ወጣት ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኛ ተመስገን ላይ በመፃፍ እውቅናን ለማግኘት ከመጣር ከላይ በአንድነት ውስጥ ከባድ እንቅስቃሴ እያደረጉ ያሉትን ምሳሌ በማድረግ ስራቸውን ማጉላት ላይ ብታተኩሩ ወይንም እነሱ ልምድ ካላቸው ፖለቲከኞች ጀርባ ሆነው ልምድ ቀስመው ዛሬ ለሀላፊነት የበቁበትን መንገድ መከተል በሳልነት መሆኑን ሳልጠቁም አላልፍም፡፡ በመጨረሻም ሰማያዊ ፓርቲ አዲስ መስመር…
ምስረታ ጀምሮ አወዛጋቢ የሆነው ሰማያዊ ፓርቲ 8 አመት ሙሉ የቀዘቀዘውን የሀገሪቱ ፖለቲካ ሚዛን በሚደፋ መልኩ ለማሞቅ ( ለማንቀሳቀስ) ጥረት እያደረገ ነው፡፡ ነገር ግን የፓርቲውን አላማና ፕሮግራም እና በፓርቲው ውስጥ ያሉት አመራሮች ከሊቀ መንበር ውጪ ያላቸው የፖለቲካ ብስለት በሰፊው ለህዝብ ስላላደረሰ አውዛጋቢነቱ እንዲቀጥል አድርጎታል ፡፡ ይህም የፓርቲውን አላማና ፕሮግራም እንዲሁም በፓርቲው ውስጥ ያሉት ወጣት አመራሮች ያላቸው የፖለቲካ ብስለት ለሰፊው ህዝብ ካልደረሰ በሀገራችን ለዘመናት ለቆየው የመጠለፍ ፖለቲካ ጭዳ ይሆናል ባይ ነኝ፡፡ በተጨማሪም እንታገልለታለን ለምትሉት ህዝብ የማሳወቅ ፓርቲው ግዴታም አለበት፡፡
ማሳሰቢያ ‘’ይልቃል አዲሱ ልደቱ” ፅሁፍ ፀሀፊ ዳዊት ሰለሞን የአንድነት ፓርቲ ልሳን የሆነው ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ኣዘጋጅ ለመሆኑ አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የአንድነት አባል ስለነገረኝ ከዚህ በታች የምጠቀመው የብእር ስሙን ሳይሆን ዳዊት የሚለውን ዋና ስሙን መሆኑን አሳውቃለሁ፡፡
መኢአድ ሲባል ኢ/ር ሀይሉ ሻወል፣ ደቡብ ህብረት ሲባል ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ፣ ኦብኮ ሲጠቀስ ዶ/ር መረራ ጉዲና… የፖለቲካ ተክለ ሰውነት ለብሰው ብቅ ይሉብናል፡፡ ይህ የፖለቲካ ተክለ ሰውነት በአንድት ውስጥም ግዝፈቱን ሳይቀንስ ተንሰራፍቶበት ቆይቷል፡፡ ይህ ማለትም አንድነት ሲባል በየደቂቃው የሚለዋወጥ አቋም ያለው ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው እና ባለመልካም ባህሪው ዶ/ር ሀይሉ አርአያ ድቅን ይሉብን ነበር እነአቶ አስራት ጣሴን አስከትለው፡፡ ወጣት ዳዊትም በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ የሚታዩ ችግሮች ብለው ከጠቀሱዋቸው መካከል የግለሰብ ተክለ ሰውነት መገንባት አንዱ ነው፡፡
እኔም የግለሰብን ተክለ ሰውነት አንዱ መስፈርት አድርጌ ፓርቲዎችን ስገመግም አንድነት አሁን ካሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ውስጥ የተሻለ ነው እንድል ያደረገኝ ከግለሰብ ትከሻ ላይ ወርዶ አበረታች የሚባል የቡድን ስራ ማክናውን ላይ በመሆኑ ነው፡፡
የተመለከትኩትን ጠንካራ ጎን ከገለፅኩ በኋላ የፓርቲው አባል የሆኑት ወጣት ዳዊት ፅሁፍ ላይ ላተኩር፡፡ ሀሳብን በነፃነት ለመግለፅ ያደረገውን ጥረት በማድነቅ ፅሁፉ መጀመሪያ ላይ የጠቀሱት የደርግ/ የኢህአፓ /የመኢሶን ፖለቲካዊ መጠላለፍ ዛሬ ላይ እንዲመጣ ወይም ዛሬ ላይ ያለው የመፈራረጅ ፖለቲካ እንዲቀጥል ታጥቀው የተነሱ ነው የሚመስለው፡፡ እንዴት! ማለት ጥሩ….. በአዲስ መስመር ከመቀጠሌ በፊት እኔ የሰማያዊ ፖርቲ አባልም ደጋፊም አለመሆኔ ሊታወቅ ይገባል፡፡
አንባቢን ለማሳመን እና ሰማያዊ ፓርቲ የወጣቶች ስብስብ መሆኑን ለማጣጣል የአቶ ልደቱ ወጣት መሆን በመጥቀሥ በጥሩ ሁኔታ እየተቀሰቀሰ ያለውን ፖለቲካ ለመጥለፍ ‹‹አዲሶቹ ጎጆ ወጪዎች ከመጀመሪያው ቤታቸው ሲወጡ በአብዛኛው ባዶ እጃቸውን አይሆኑም፣የእናት ፓርቲያቸውን የፖለቲካ ፕሮግራም፣አደረጃጀትና አባል ይዘው ሹልክ ይላሉ፡፡ለዚህ እንደምሳሌ ኢዴፓና ሰማያዊ ፓርቲን መውሰድ ይቻላል፡፡›› ይሞክራሉ፡፡ እኔም አንድ የመጥለፉ መንገድ ልከተልና ፀሀፊውን ልጠይቀው፡፡ ቅንጅት የአራት ፓርቲዎች ጥምረት ነው፡፡ መሪዎቹ ታስረው ሲፈቱ በጋራ መቆም አቃታቸውና የየራሳቸውን ደጋፊና አባል በመያዝ ለአራት ተሰነጣጠቁ፡፡ከግንቦት 7 በስተቀር ሁሉም የሰላማዊ ትግል መርጦ የቅንጅቱን መንፈስና ፕሮግራም ለማስቀጠል በያለበት ይንቀሳቀሳል፡፡ ከነዚህ ውስጥም አንድነት አንዱ በመሆኑ የእናት ድርጀቱን አባል ፕሮግራም ይዞ ሹልክ አለ ማለት ነው ወይስ አንድነት የተለየ ፕሮግራም አረቀቀ? ይህን ለመመለስ የቅንጅትንም የአንድነት በደንብ ፕሮግራሞች ማየት ያስፈልጋል እንዳትረሳው!
የሰማዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር ላይ ያስቀመጠው ቅሬታ / ግን ሰይጣናዊ ቅናት ብለው በትክክል ይገልፀዋል/ ጠቅለል አርጌ ለመግለፀ በሁለት መክፈል እፈልጋለሁ፡፡ ሊቀመንበሩ ላይ የቀረበው ቅሬታ ለፖለቲካው በማሰብ በሚል እና ፀሀፊው ጎልቶ ለመውጣት ባለው ጉጉት የሚከተላቸው መንገዶች በሚሉ ፡፡
ለፖለቲካው በማሰብ
ኢ/ር ይልቃል /የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር/ “ፓርቲዎች አሉ ብለን አናምንም ተባበሩ የምትለን ከማን ጋር ነው ? መድረክ ምን ሰራ አንድነትና መድረክ እየተባሉ አይደለም? አንድነት ውስጥ የገባው ብርሃን ወጥቷል እኛ ከማን ጋር እንተባበር ? ብለዋል ብሎ ወጣት ዳዊት ይኮንናል፡፡ የኢ/ር ይልቃል ንግግር ላይ ያለውን ስህተት ለማሳየት ፓርቲዎቹ የሰሩትን ምንም መረጃ ማቅረብ ስላልቻለ በደፈናው በህብረት ለመስራት አንፈልግም ብለዋል ሲል ተንከባሎ ያልፋል፡፡ የመድረክ አባል ፓርቲዎች የደቡብ ህብረት ከፕ/ር በየነ ሳምሶናት ውስጥ መውጣት ሳይችል፣ ኦፍዴን ከአቶ ቡልቻ የግል ንብረትነት ሳያልፍ፣ ኦብኮ ከዶ/ር መራራ የኮሜዲ ምሽት ሳይላቀቅ ፣አረና አባላቱ በነፃ ዝውውር ለሰማያዊ ፓርቲ እየፈረሙ ባሉበት ሰአት እና አንድነት በኣዛውንቶችና በወጣቶች መሀክል በሚደረግ ገመድ ጉተታ ፖለቲካ ውስጥ ነው ያለው ስለዚህ ከማን ጋር በህብረት ይስራ ነው የሚባለው፡፡ በተጨማሪም ብርሀንም ከአንድነት የወጣው ገመድ የጉተታ ውጤት ይዞት የሚመጣው ጦስ አስግቶት ነው፡፡ ታዛቢ ስላለ እውነቱ ይህ መሆኑን መግለፅ ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ የተቀረበው ቅሬታ ለፖለቲካው በማሰብ አደለም ለማለት እደፍራለሁ፡፡
በተጨማሪም አንድነትን ጨምሮ ሁሉም የመድረክ ፓርቲዎች ጥርት ያለ የፖለቲካ ፕሮግራም ስለሌላቸው መስማማት አልቻሉም ፡፡ ይህንን ስል በስሜት አለመሆኑን ለማስገንዘብ ሁለት ምሳሌ ልጥቀስ፡፡ የመሬት ጥያቄና የመገንጠል መብት ፓርቲዎቹ ከግንባርነት እንዳያልፉ ማነቆ ሆነው ስራ እዳይሰሩ ያደረጋቸውን ብቻ ማንሳት በቂ ነው፡፡ ይህም እውነት ሲገለጽ በሰማያዊ ፓርቲ ፕሮግራም ላይ የተቀረበው ቅሬታ ለፖለቲካው በማሰብ አይደለም ለማለት እገደዳለሁ፡፡
ጎልቶ ለመውጣት የሚደረግ ጥረት
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንድነት ከላይ እንደጠቀስኩት ከግለሰብ ስብእና ራሱን በማፅዳት የቡድን ስራን በመጀመር የሚያበረታታ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡ ይህም የቡድን እንቅስቃሴ ባለፉት ግዚያት እንደተመለከትነው በተለያዩ የክልል ከተሞች በመንቀሳቀስ የቀዘቀዘው የህዝብ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ዳግም እንዲያንሰራራ ሚዛን የሚደፋ አስተዋፆ አድረጓል፡፡ ለዚህም አበረታች ጅማሮ ከፊትም ከኋላም በመሆን ከፍተኛ አስተዎ ያደጉትን ግርማ ፣ዳንኤል እና በላይን የመሰሉ ወጣት ፖለቲከኞችን ማመስገን ያስፈልጋል፡፡ በዛውም ልክ ይልቃል ጎልቶ ለመውጣት ይፈልጋል ተብሎ እንደተከሰሰው በአንድነት ህዝባዊ ንቅናቄም ውስጥም በበርካታ ወጣቶች ላይ ጎልቶ የመታየት ፍላጎት ሲከሰት ከርሟል፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዱ ወጣት ዳዊት ይግኝበታል፡፡ እንዴት የሚል ጥያቄ ከተነሳም መልሱን ክዚህ በፊት ወጣቱ የሚያድጋቸውን ጎልቶ ለመውጣት የሚደረግ ድርጊቶች ላሳይ፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አንድነት ፓርቲ ውስጥ የተመለከታቸውን ህፀፆች እንደጋዜጠኝነቱ እንዲታረሙ በበሳል ብእሩ ሲጠቁም የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የጋዜጠኛውን ጥቆማ በመቀበል የታዩትን ችግሮች ለማረም ደፋ ቀና ብለዋል፡፡ ነገር ግን ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ የተባለው ብሂል በወጣቱ ዳዊት ላይ ተተግብሮ ‹‹ ተመስገን ደሳለኝ ሲያዳልጠው›› በሚል ጽኁፍ በአደባባይ ፓርቲውን ለምን ነካ ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት እፍኝ እውቅና ለማግኘት ሲታገል መድከሙ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ ይህ ተግባር በተመስገን ላይ ብቻ የተገደበ እይደለም ፡፡ ብዙ መጥቀስ ይቻላል ነገር ግን ዝም በመባሉ ያሸነፈ ስለመሰለው በተመሣሳይ ላሞኛችሁ አይናችሁን ጨፍሁ ብሎ በኢ/ር ይልቃል ላይ እንዲህ ሲዘምት ጎልቶ ለመውጣት በሚደረግ ጥረት የሚቀዘቅዘው የወጣቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ስላሳሰበኝ ነው ይህን ጽሁፍ ለመጻፍ የተገደድኩት፡፡
በአጠቃለይ የወጣቱ ፅሁፍ ለሀገራችን ፖለቲካ በማሰብ የቀረበ ሀሳብ ሳይሆን ጎልቶ ለመውጣት የሚደረግ ጥረት በመሆኑ የተጀመረው የህዝብን የማንቃት ስራ አዳክሞ ሀገሪቱን በአንባገነንነት ለሚመራው ኢህአዴግ ነው የሚጠቅመው፡፡ ስለዚህ ወጣት ዳዊት ገና ብቅ ብቅ የሚሉ ወጣት ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኛ ተመስገን ላይ በመፃፍ እውቅናን ለማግኘት ከመጣር ከላይ በአንድነት ውስጥ ከባድ እንቅስቃሴ እያደረጉ ያሉትን ምሳሌ በማድረግ ስራቸውን ማጉላት ላይ ብታተኩሩ ወይንም እነሱ ልምድ ካላቸው ፖለቲከኞች ጀርባ ሆነው ልምድ ቀስመው ዛሬ ለሀላፊነት የበቁበትን መንገድ መከተል በሳልነት መሆኑን ሳልጠቁም አላልፍም፡፡ በመጨረሻም ሰማያዊ ፓርቲ አዲስ መስመር…
ምስረታ ጀምሮ አወዛጋቢ የሆነው ሰማያዊ ፓርቲ 8 አመት ሙሉ የቀዘቀዘውን የሀገሪቱ ፖለቲካ ሚዛን በሚደፋ መልኩ ለማሞቅ ( ለማንቀሳቀስ) ጥረት እያደረገ ነው፡፡ ነገር ግን የፓርቲውን አላማና ፕሮግራም እና በፓርቲው ውስጥ ያሉት አመራሮች ከሊቀ መንበር ውጪ ያላቸው የፖለቲካ ብስለት በሰፊው ለህዝብ ስላላደረሰ አውዛጋቢነቱ እንዲቀጥል አድርጎታል ፡፡ ይህም የፓርቲውን አላማና ፕሮግራም እንዲሁም በፓርቲው ውስጥ ያሉት ወጣት አመራሮች ያላቸው የፖለቲካ ብስለት ለሰፊው ህዝብ ካልደረሰ በሀገራችን ለዘመናት ለቆየው የመጠለፍ ፖለቲካ ጭዳ ይሆናል ባይ ነኝ፡፡ በተጨማሪም እንታገልለታለን ለምትሉት ህዝብ የማሳወቅ ፓርቲው ግዴታም አለበት፡፡
በአንዋር መስጂድ ፖሊስ ሙስሊም ሴቶች ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፈጸመ! ጁምአ
August 23, 2013
ድምፃችን ይሰማ
ጭንቅላታቸው የተፈነከተና ደም ይፈሳቸው የነበሩ ሴቶች ታይተዋል!
ጥቂት የማይባሉ እናቶችና እህቶች ሰላታቸውን ሳይሰግዱ ወደ ቤታቸው ለመመለስ ተገደዋል!
ዛሬ የጅምአን ሰላት ለመስገድ በተገኙ እናቶች ላይ ፖሊስ ድብደባ መፈጸሙ ታወቀ፡፡ በመርካቶ አንዋር መስጂድ የዛሬውን የጁምአ ሰላት ለመፈጸም የተገኙ በርካታ እናቶችና እህቶች በፖሊስ አባላት ከፍተኛ ድብደባ ተፈጸመባቸው፡፡ እነዚሁ ለጸሎት የተሰባሰቡ እናቶች ድብደባ የተፈጸመባቸው ከመስጂዱ ግቢ ውጪ አንጥፋችሁ መስገድ አትችሉም በሚል ነው፡፡
ታላቁ አንዋር መስጂድና ሌሎችም መስጂዶች በጁምአ እለት የሚመጣውን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ማስተናገድ ስለሚሳናቸውና ስለሚሞሉ ህብረተሰቡ ውጪ አንጥፎ መስገዱ ባለፉት 15 ዓመታት የተለመደና የሚታወቅ ሀቅ ቢሆንም በሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ ብሄራዊ ጭቆናን እያሰፈነ ያለው መንግስት ሙስሊሞችን በሁሉም አቅጣጫ ለማጥቃት በማለም የተለያዩ ምክንያቶችን በመደርደር በተለይም ሴቶች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ቀጥሎበታል፡፡
በዛሬው ድብደባ ጭንቅላታቸው የተፈነከተና ደም ይፈሳቸው የነበሩ ሴቶች እንደነበሩ የታወቀ ሲሆን ጥቂት የማይባሉ እናቶችና እህቶች ሰላታቸውን ሳይሰግዱ ወደ ቤታቸው ለመመለስ ተገደዋል፡፡ መንግስት የሃይማኖት አክራሪነትን እታገላለሁ በሚል ስም በሙስሊሙ ላይ ብሔራዊ ጭቆና በማስፈን ላይ ይገኛል፡፡ የዚህ ጭቆና ዒላዎችም ልክ ዛሬ እንደታየው አረጋውያን እናቶችና እህቶች ሆነዋል፡፡
የእምነት ነጻነትን አክብሪያለሁ እያለ ደጋግሞ በሚዲያ የሚናገረው መንግስት በሕገ መንግስቱ የተቀመጡትን የእምነት ነጻነት መብቶች በመጣስ ሙስሊሙ ላይ ከፍተኛ በደል በማድረስ ላይ ይገኛል፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብ የራሱ የእምት ተቋም እንዳይኖረው ከማድረግ አንስቶ አዲስ እምነት በሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ በኃይል መጫን፣ የሙስሊሙን ማህበረሰብ መሪዎች ማሰርና ማሰቃየት፣ የመብት ጥያቄ ያነሱ ሰላማዊና ያልታጠቁ ዜጎችን መግደል፣ መስጂዶችን ማሸግ፣ ኢማሞችን ያለ ሕዝቡ ፍላጎት ከስራቸው ማፈናቀልና በራሱ ፍላጎት መንግስታዊ ኢማሞችን መተካት እና ሌሎችም በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሊፈጸሙ የማይችሉ ተግባራትን መንግስት ያለ ምንም ሀፍረት ሲፈጽም ቆይቷል፡፡
አሁን ደግሞ በክልሎች ሲካሄድ እንደነበረው ሁሉ ሙስሊሙን ሕብረተሰብ ከሰላት ለማቀብና ለማሸማቀቅ ለመስገድ ወደ መስጂድ የሄዱ ሙስሊሞችን ለጸሎት በተቀመጡበት ድብደባ ሲፈጸምባቸው እየተመለከትን ነው፡፡ የዚህ አይነቱ ተግባር በኢትዮጵያ ታሪክ ቢያንስ ባለፉት 90 ዓመታት እንኳ ያልታየ ድርጊት የእምነት ነጻነት በሕገ መንግስት ደረጃ በተደነገበት በዚህ ወቅት እየተፈጸመ መሆኑ ሙስሊሙ ህብረተሰብ የመንግስትን አላማና ግብ በአንክሮ አንዲያጤነው የሚጋብዝ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት በደሴ ሸዋ በር መስጂድ መስጂድ የሞላባቸው የከተማው ሙስሊሞች ውጪ አንጥፋችሁ ሰግዳቹሀል በሚል ፖሊስ ከፍተኛ ጥቃት ሰንዝሮ በርካቶችን ለእስርና አሰቃቂ ድብዳባ መዳረጉ ይታወሳል፡፡
መንግስት መሰል ሁኔታዎችን ኹከት ለመፍጠር የሚጠቀምባቸው በመሆኑ ሁኔታዎችን በትእግስት ከማሳለፍ በዘለለ ድርጊቱ ሲፈጸም ፎቶ ግራፍና ቪዲዮ ማንሳት ሊዘነጋ የማይገባ ተግባር መሆኑን ማስታወስ ያሻል፡፡
አላሁ አክበር!
ECADF Ethiopian News

በአሜሪካ ግቢ ቦምብ እላያችን ላይ ሳይፈነዳብን ተገኘ
ምስጋና ለኢትዬጲያ ፌደራል ፖሊስ እና ለብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ኤጀንሲ ጥምር የጸረ ሽብር ቡድን ግብረ ሃይል
በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በተለምዶ በአሜሪካ ግቢ ራስ ስዩም ሆቴል አጠገብ ወደ አርባምንጭ ከተማ ጭነት የሚጫንበት ቦታ አካባቢ በሚገኘው ራህመት ኤጀንሲ በር ላይ ኮድ 3 የታርጋ ቁጥር 73189 በሆነ አንድ |የጭነት ማመላለሻ አይሱዙ ጎማ ስር የአጅ ቦምብ ተገኘ ተባለላቹ፡፡፤
ይህን የእጅ ቦምብ የአዲስ አበባ ከተማ መደበኛ ፖሊሶች ቀደም ብለው በእጃቸው ይዘውት እንደነበር የአይን እማኞች ገልጸዋል፡፤የእጅ ቦምቡን ጠዋት ይዘውት ከነበሩት ሁለት ፖሊሶች መካከል የአንዱ ፎቶ ከዚህ በታች ተያይዞ ቀርቧል|፡፡ሙስሊሙ የመረጃ ሰው ሆኗል፡፡አልሃምዱሊላህ
ይህ ቦምብ አፈንጂው እና ቦምባ አምካኞች ያደረጉት ትንቅንቅ አንድ ወንድም ያደረሰኝን መረጃ ላካፍላችሁ፡፡የተቀረውን መረጃ በቦታው ከነበሩ እና ከኢቲቪ ማጣራት ትችላላችሁ
አንድ ግለሰብ ቦምብ ይዞ በመምጣት አንድ የጭነት መኪና ጎማ ስር ቦምቡን አስቀምጦ ዞር ይላል፡፤ በመቀጠልም ይህ ግለሰብ ከቆይታዎች ቡሃላ ተመልሶ በመምጣት እዛው አካባቢ ይቆማል፡፡ በመቀጠልም ፖሊስ ይህን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ያውለዋል፡፡ከዛ ፖሊስ ይህን ግለሰብ ሲፈትሸው ሌላም ቦምቦች በኪሱ ስር ያገኛሉ፡፡ ከዛ የፌደራል ፖሊስ እና የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ኤጀንሲ የጸረ ሽብር ግብረሃይል ይህን አሸባሪ ግለሰብ በህዝብ እና በንብረት ላይ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር አዋሉት፡፤ ከዛ የፈንጂ አምካኝ ግብረሃይል መጣና መኪናው ጎማ ስር የተቀመጠውን ቦምብ እንዳይፈነዳ በጥንቃቄ በማድረግ አክሸፈው፡፤ከዛ በቃ ድራማው በሚገርም ሁኔታ በመጠናቀቁ ቀረጻ ተካሂዶለታል፡፡በጥሞና ስላነበባችሁልኝ አመሰግናለው
ቆይ ትንሽ ልጨምርላችሁ ይህ አሸባሪ ግለሰብ እራሱ ያስቀመጠው ቦምብ ጋር በመምጣት መፍንዳት እና አለመፈንዳቱን የሚጠባበቀው ምንኛ አስገራሚ አሻባሪ ነው???? ቀጥሎም ለሌላ ተልኮ የሚሆን ቦምቦችን በኪሶ ሸክፎ ይዞ ነበር፡፤ይህንንም አደገኛ ሊፈጸም የነበረውን የሽብር ጥቃት በማስመለከት ለኢቲቪ ዜና የሚሆን ድራማ ይህ አሸባሪ ግለሰብ ከፌደራል ፖሊስ እና ከብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ኤጀንሲ የጸረ ሽብር ግብረ ሃይሉ ጋር በመሆን ሲከውን እንደነበር የአይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ የዚህን ሙሉ ዜና ዝርዝር ማታ ኢቲቪ ዜና ላይ ይጠብቁ:;
ከዚህ ቀደም በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያም ተመሳሳይ ጠቀጣጣይ የሆኑ ሁለት ስሊንደሮች ተቀምጠው መገኘታቸው ኢቲቪ ዘግቦልን ነበር፡፡ደሞ ሌላ ቀን ምን አይነት ነገር መያዡን እንሰማ ይሆን???? ፡፡
ምናለ ኢትዬጲያ ሃገሬ ለአለም ሰላም ሁሌም በምታደርገው ጥረት የምትደነቅ በመሆኗ እንዲህ አይነት የፀረ ሽብር ግብረ ሃይሏን ችሎታ ለሌሎች ሃገሮችም ልምዷን ብታካፍል እና ቦምቦች ሳይፈነዱባቸው ሁሌም ከነአሸባሪው በቁጥጥር ስር እንዲ ያውሉ ብትረዳቸው ?????
እኔስ ምንም አልልም ግን ብቻ ይሄ ድራማ እንዲ እያጃጃለን አንድ ቀን የምር አፈንድተውት እንዳይጨርሱን እሰጋለው!!!
ለማንኛውም ቦንቦቹ ሳይፈነዱ በቁጥጥር ስር ስለዋሉ አልሃምዱሊላህ በዚህኛው ድራማ ሂወታችንን አልቀጠፉብንም፡፡
አላህ የኢትዬጲያን ህዝብ
ለድራማ ተብሎ ከሚደረስ ጥቃት ይጠብቅልን!!!!
ድል ለኢትዬጲያ
በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በተለምዶ በአሜሪካ ግቢ ራስ ስዩም ሆቴል አጠገብ ወደ አርባምንጭ ከተማ ጭነት የሚጫንበት ቦታ አካባቢ በሚገኘው ራህመት ኤጀንሲ በር ላይ ኮድ 3 የታርጋ ቁጥር 73189 በሆነ አንድ |የጭነት ማመላለሻ አይሱዙ ጎማ ስር የአጅ ቦምብ ተገኘ ተባለላቹ፡፡፤
ይህን የእጅ ቦምብ የአዲስ አበባ ከተማ መደበኛ ፖሊሶች ቀደም ብለው በእጃቸው ይዘውት እንደነበር የአይን እማኞች ገልጸዋል፡፤የእጅ ቦምቡን ጠዋት ይዘውት ከነበሩት ሁለት ፖሊሶች መካከል የአንዱ ፎቶ ከዚህ በታች ተያይዞ ቀርቧል|፡፡ሙስሊሙ የመረጃ ሰው ሆኗል፡፡አልሃምዱሊላህ
ይህ ቦምብ አፈንጂው እና ቦምባ አምካኞች ያደረጉት ትንቅንቅ አንድ ወንድም ያደረሰኝን መረጃ ላካፍላችሁ፡፡የተቀረውን መረጃ በቦታው ከነበሩ እና ከኢቲቪ ማጣራት ትችላላችሁአንድ ግለሰብ ቦምብ ይዞ በመምጣት አንድ የጭነት መኪና ጎማ ስር ቦምቡን አስቀምጦ ዞር ይላል፡፤ በመቀጠልም ይህ ግለሰብ ከቆይታዎች ቡሃላ ተመልሶ በመምጣት እዛው አካባቢ ይቆማል፡፡ በመቀጠልም ፖሊስ ይህን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ያውለዋል፡፡ከዛ ፖሊስ ይህን ግለሰብ ሲፈትሸው ሌላም ቦምቦች በኪሱ ስር ያገኛሉ፡፡ ከዛ የፌደራል ፖሊስ እና የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ኤጀንሲ የጸረ ሽብር ግብረሃይል ይህን አሸባሪ ግለሰብ በህዝብ እና በንብረት ላይ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር አዋሉት፡፤ ከዛ የፈንጂ አምካኝ ግብረሃይል መጣና መኪናው ጎማ ስር የተቀመጠውን ቦምብ እንዳይፈነዳ በጥንቃቄ በማድረግ አክሸፈው፡፤ከዛ በቃ ድራማው በሚገርም ሁኔታ በመጠናቀቁ ቀረጻ ተካሂዶለታል፡፡በጥሞና ስላነበባችሁልኝ አመሰግናለው
ቆይ ትንሽ ልጨምርላችሁ ይህ አሸባሪ ግለሰብ እራሱ ያስቀመጠው ቦምብ ጋር በመምጣት መፍንዳት እና አለመፈንዳቱን የሚጠባበቀው ምንኛ አስገራሚ አሻባሪ ነው???? ቀጥሎም ለሌላ ተልኮ የሚሆን ቦምቦችን በኪሶ ሸክፎ ይዞ ነበር፡፤ይህንንም አደገኛ ሊፈጸም የነበረውን የሽብር ጥቃት በማስመለከት ለኢቲቪ ዜና የሚሆን ድራማ ይህ አሸባሪ ግለሰብ ከፌደራል ፖሊስ እና ከብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ኤጀንሲ የጸረ ሽብር ግብረ ሃይሉ ጋር በመሆን ሲከውን እንደነበር የአይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ የዚህን ሙሉ ዜና ዝርዝር ማታ ኢቲቪ ዜና ላይ ይጠብቁ:;
ከዚህ ቀደም በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያም ተመሳሳይ ጠቀጣጣይ የሆኑ ሁለት ስሊንደሮች ተቀምጠው መገኘታቸው ኢቲቪ ዘግቦልን ነበር፡፡ደሞ ሌላ ቀን ምን አይነት ነገር መያዡን እንሰማ ይሆን???? ፡፡
ምናለ ኢትዬጲያ ሃገሬ ለአለም ሰላም ሁሌም በምታደርገው ጥረት የምትደነቅ በመሆኗ እንዲህ አይነት የፀረ ሽብር ግብረ ሃይሏን ችሎታ ለሌሎች ሃገሮችም ልምዷን ብታካፍል እና ቦምቦች ሳይፈነዱባቸው ሁሌም ከነአሸባሪው በቁጥጥር ስር እንዲ ያውሉ ብትረዳቸው ?????
እኔስ ምንም አልልም ግን ብቻ ይሄ ድራማ እንዲ እያጃጃለን አንድ ቀን የምር አፈንድተውት እንዳይጨርሱን እሰጋለው!!!
ለማንኛውም ቦንቦቹ ሳይፈነዱ በቁጥጥር ስር ስለዋሉ አልሃምዱሊላህ በዚህኛው ድራማ ሂወታችንን አልቀጠፉብንም፡፡
አላህ የኢትዬጲያን ህዝብ
ለድራማ ተብሎ ከሚደረስ ጥቃት ይጠብቅልን!!!!
ድል ለኢትዬጲያ
Ethiopia: Device found at Addis Ababa’s international airport was not an explosive
August 22, 2013 (ADDIS ABABA) - A senior government official said on Thursday that a device found at Addis Ababa’s international airport was not an explosive, as was recently was reported by Sudan Tribune and other media outlets.
“The device was not an explosive or type of bomb but just a flammable cylinder gas”, communication minister Shimels Kemal told Sudan Tribune, adding that a counter-terrorism team had been established to deal with the incident.
Kemal said the situation is under investigation and no suspect has yet been arrested.
Airport authorities today similarly confirmed that the devices found were gas cylinders.
The two gas cylinders, which could potentially explode if they caught on fire, were first found by airport janitors.
The two devices were found around the departure terminal of the country’s largest airport.
Airport officials said details of the incident will be announced once the investigation is complete, declining to provide further comment on the matter.
The investigation team is yet to determine if the devices were deliberately deposited at the airport in order to commit a terrorist attack.
Addis Ababa Bole International Airport is one of the continent’s busiest airports, with a current traffic movement of nearly 2 million passengers per year, according to Ethiopian Airports Enterprise (EAE).
EAE has finalised an expansion and upgrade project at the airport which would enable it to park more passenger jets at a time.
The airport has been serving to the East African nation as an international gate way for over 40 years.
Subscribe to:
Posts (Atom)